ያንጎ ግሩፕ ለ2026 የፌሎውሺፕ መርሃ ግብር ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የ24 ተሳታፊዎችን ዝርዝር ይፋ አደረገ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ያንጎ ግሩፕ ከስድስት የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡና ከ600 በላይ ከሚሆኑ አመልካቾች መካከል የተመረጡ 24 የ2026 የያንጎ ፌሎውሺፕ ፕሮግራም ተሳታፊዎችን ስም ዝርዝር በይፋ አስታውቋል።

እነዚህ ተሳታፊዎች በ12 ሳምንታት የቆይታ ጊዜያቸው የቴክኒክ ክህሎታቸውን በመጠቀም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረቱ የፈጠራ ስራዎችን የሚያከናውኑ ሲሆን በመጨረሻም በአቢጃን በሚዘጋጅ ልዩ መድረክ ላይ ውጤታቸውን ያቀርባሉ።

ተሳታፊዎቹ ከኢትዮጵያ፣ ከኮት ዲቯር፣ ከዛምቢያ፣ ከሴኔጋል፣ ከሞዛምቢክ እና ከጋና የመጡ ናቸው።

መርሃ ግብሩ በዘንድሮው የጥናት ዓመት ተደራሽነቱን በማስፋት ከሁለት ወደ ስድስት ሀገራት ማደጉ ተገልጿል።

የዘንድሮው ትኩረትም በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ወይም በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ተግባራዊ አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ነው።

በዚህም እንደ ጤና፣ የኃይል ቁጥጥር፣ የትራፊክ ማሻሻያ እና የትምህርት መፍትሄዎችን ያካተቱ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለዕይታ ይቀርባሉ።

ይህ የፌሎውሺፕ መርሃ ግብር በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን ችግር ፈቺ ጥናቶችን ማካተት፣ የምርት ልማት እና የመጨረሻ የአቀራረብ ደረጃዎችን ይይዛል።

በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ በሚከናወነው የዲሞ ደይ ዝግጅት ተሳታፊዎች ስራቸውን ለባለሙያዎች የሚያቀርቡ ሲሆን ተስፋ ላላቸው ፕሮጀክቶችም የፋይናንስ ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚችል ተጠቁሟል።

የያንጎ ግሩፕ ዋና የንግድ ጉዳዮች ኃላፊ አዴኒዪ አዴባዮ እንደገለጹት ፕሮግራሙ በአካባቢው የቴክኖሎጂ እድገት ላይ የሚደረግ የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንት ነው።

ተቋሙ የአፍሪካን የቴክኖሎጂ ፍላጎት የሚፈቱ የፈጠራ ባለቤቶችን ለመደገፍ እና ከአንድ ሀገር በላይ ሊሰሩ የሚችሉ ምርቶች እንዲበለጽጉ ለማገዝ ፍላጎት እንዳለውም አክለዋል።

በአሁኑ ወቅት አፍሪካ ከ2.5 ሚሊዮን በላይ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሂሳብ (STEM) ባለሙያዎች እጥረት እንዳለባት የዓለም ባንክ መረጃ ያሳያል።

በመሆኑም ይህ ፕሮግራም በተግባራዊ ስልጠና እና በባለሙያዎች ምክር የታገዘ በመሆኑ ለዘርፉ እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

ቀደም ሲል የነበሩ ተሳታፊዎች በተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች ላይ ውጤታማ ስራዎችን የሰሩ ሲሆን አንዳንዶቹም የራሳቸውን የዲጂታል ምርቶችና ኩባንያዎች መመስረት መቻላቸው ተመላክቷል።

ያንጎ ግሩፕ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ወደ እለት ተእለት አገልግሎት በመቀየር የሚታወቅ ዓለም አቀፍ ኩባንያ ነው።

ተቋሙ በትራንስፖርት፣ በማድረስ፣ በመዝናኛ እና በሌሎች ዲጂታል ዘርፎች በአፍሪካና በተለያዩ የዓለም ክፍሎች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

#YangoGroup #YangoFellowship #Technology #AfricaTech #AI #Innovation #STEM #EthiopiaNews #GetuTemesgen #Getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: