የጥናታዊ ፅሑፍ እና የውይይት መድረክ ነገ ማክሰኞ ይካሄዳል
አዲስ አበባ ከትላንት እስከ ዛሬ ያሳለፈችበት የከተማነት እድገት ጉዞ፣ በሁሉም መስክ እየተከናወኑ ያሉ ከተማን የማደስና የልማት ሥራዎች፣ መልካም እድሎችና ተግዳሮቶች በመድረኩ እንደሚወሱበትና ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችና ልምዶች በስፋት እንደሚቀርቡበት ተገልጿል፡፡
የናሽናል ሚዲያ አክስዮን ማህበር ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘካርያስ ብርሃኑ እንደገለፁት NBC Ethiopia TV በመንግስትና በህዝብ መካከል ድልድይ ሆኖ በማገልገል ባለው ትልም በአዲስ አበባ ሁለንተናዊ ልማት ዙሪያ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በአንድ መድረክ ዙሪያ እንዲመክሩ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ሲሆን ሁሉም ወገን በባለቤትነት የሚሳተፍበትና የሚወያይበት ነው፡፡
የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ምሁራንና ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎች፣ የሚዲያና የኪነጥበብ ሰዎች በሚገኙበት በዚህ መድረክ አንጋፋ የመስኩ ምሁራን የመነሻ ጽሁፍ ያቀርባሉ፡፡
ማክሰኞ ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም በአድዋ ድል ሙዚየም ሁለገብ አዳራሽ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በሚካሄደው የውይይት መድረክ ተዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚገኙም ታውቋል፡፡



Source: FastMereja









No comments yet.