የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆርሙዝን “እንደ ጦር መሣሪያ” መጠቀም እንደማይገባ አስጠነቀቁ

- Advertisement -
Sidebar AD

የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን ማክሰኞ ዕለት ለቀጣናዊ መረጋጋትም ሆነ ለዓለም አቀፉ ምጣኔ ኃብት ሲባል ሆርሙዝን እንደ ጦር መሣሪያ መጠቀም እንደማይገባ አስጠነቀቁ።
ፊዳን ከኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሀመድ ቢን አብዱራህማን ቢን ጃሲም አልታኒ ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ “በባህረ ሰላጤው ላይ እያጋጠመን ያለው ችግር በምንም መልኩ የጋዛ ጉዳይ እንዲረሳ ሊያደርገው አይገባም” ብለዋል።
ፊዳን የእስራኤል ተስፋፊነት በቀጣናው “መረጋጋት እና ደህንነት ላይ” ዋነኛ ስጋት ሆኗል ብለዋል።
በኢራን ላይ የተካሄደው ጦርነት የዓለም የኢነርጂ እና የሸቀጦችን ገበያ አውኳል። አገሪቱ ለነዳጅ ጭነት ወሳኝ የሆነውን የሆርሙዝ ወሽመጥን መዝጋት ብቻ ሳይሆን ለማለፍ የሞከሩ ነዳጅ ጫን መርከቦች ላይ ጥቃት ፈጽማለች።

ዶናልድ ትራምፕ በአውሮፓ የሚገኙ የአሜሪካ አጋሮች የባሕር ወሽመጡን እንዲጠብቁ ጫና ለማሳደር ቢሞክሩም እስካሁን ድረስ አልተሳካላቸውም።
አሜሪካ የሆርሙዝ ወሽመጥን እንደገና ለመክፈት የምታደርገውን ጥረት ካልደገፉ “የኔቶ የወደፊት ዕጣ ፈንታ በጣም መጥፎ” እንደሚሆን አስጠንቅቀው ነበር።
በባሕረ ሰላጤው የተፈጠረው የመርከብ ጉዞ መስተጓጎል የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ከፍ እንዲል አድርጓል።
ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት አንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ከነበረበት ከ70 የአሜሪካ ዶላር አሁን ከ100 የአሜሪካ ዶላር በላይ እንዲደርስ አድርጓል።

BBC




Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1