እናታቸው አላቀፈቻችውም፤ ጡትም አልጠቡም

- Advertisement -
Sidebar AD

🙏

ወላጆቻቸው ልጅ አጥተው ሠላሳ ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል፡፡ አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ አንድ ቀን አቅሌሲያ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከሥዕለ ሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማጸን ታላቅ ክብር ያለው ልጅ እንደምትወልድ የሚናገር ድምጽ ሰማች፡፡ በመጋቢት 29 ቀን ፀንሳ በታኅሣሥ 29 ቀን ደም ግባቱ እጅግ የሚያምር ወንድ ልጅ ግብጽ ንሂሳ በምትባል ቦታ ወለደች፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በሰው አምሳል መጥቶ “የዚህ ልጅሽ ስሙ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ይሁን” አላት፡፡ ሕፃኑ ከእናቱ ጭን ወርዶ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ሦስት ጊዜ ሰገደ፡፡ “ከጨለማ ወደ ብርሃን ለአወጣኸኝ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን” አለ፡፡ ከዚህ በኋላ ፡፡

ሦስት ዓመት ሲሞላቸውም ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ ሕፃኑን ከእናቱ ክንድ ወስዶ እስከ ሰባቱ ሰማይ አውጥቶ በሥሉስ ቅዱስ ፊት አቅርቦት አስባረከው፡፡ እመቤታችን፣ ቅዱሳንም ሁሉ ባረኩት፡፡ አምላካችን እግዚአብሔርም አጸናው አበረታው፡፡ ከዚህም በኋላ መልአኩ አባ ዘመደ ብርሃን ወዳለበት ገዳም አወረደው እርሱም አስተምሮ ካሳደገው በኋላ ዲቁና በኋላም ምንኩስናና ቅስና ሰጠው፡፡ ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በጾም በጸሎት ተጠምደው በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመሩ፡፡ የተአምራትና የፈውስ ሀብት ተሰጣቸው፡፡ ከሰው ተለይተው ከአናብስትና ከአናብርት ጋር እንዲኖሩ፣ እንስሳቱም የእግራቸውን ትቢያ እየላሱ እንደሚኖሩ ነገራቸው፡፡

ሰውነታቸውም ሁሉ በጠጉር ተሸፈነ፡፡ በፍጹም ተጋድሎም ከኖሩ በኋላ በቀንና በሌሊት የክርስቶስን መከራ እያሰቡ ስለኃጥአንም ጥፋት እንባቸውን እያፈሰሱ ይጸልዩ ነበር፡፡ ሦስት መቶ ዓመት ሲሆናቸውም ቅዱስ ገብርኤል በነፋስ ሠረገላ ጭኖ ከ60 አንበሶችና ከ60 ነብሮች ጋር ወደ ኢትዮጵያ አምጥቶ ምድረ ከብድ አደረሳቸው፡፡ ደብር ቅዱስ ወደሚባለው ዝቋላም ሔደው የኢትዮጵያን ሕዝብ ማርልኝ ብለው ለአንድ መቶ ዓመት ተዘቅዝቀው ስጋቸው እስኪያልቅ ጸልየዋል፡፡ ጌታችንም መጥቶ ኢትዮጵያን ምሬልሀለሁ ብሎ ታላቅ ቃል ኪዳን ሰጣቸው፡፡ አባታችን በሀገራችን 262 ዓመታት ኖረው በተወለዱ በ562 ዓመታቸው በዕለተ እሁድ አርፈዋል፡፡ በቅዱሳኑ ምልጃ ያመንን ገዳማውያንን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2