ሀገር አቀፍ የባህልና ቋንቋ ሳምንት ሊከበር ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I ከግንቦት 06/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሀገር አቀፍ የባህልና ቋንቋ ሳምንት በአዲስ አበባ በአዲሱ የሚኒስትሮች ቢሮ (በቀድሞ ባህል ማዕከል) እንደሚካሄድ ተገለጸ።

ይህ ዝግጅት “የባህል ልማት ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም የኢትዮጵያን ብዝሃ ባህልና ቋንቋ በማስተዋወቅ ብሄራዊ አንድነትን እና ማህበራዊ ትስስርን ማጠናከር ነው። መንግስት የባህልና ቋንቋ ፖሊሲን ወደ መሬት ለማውረድና ትውልድን በባህል ለመቅረጽ እየሰራ ባለው ስትራቴጂ መሰረት የተዘጋጀ መድረክ መሆኑም ተጠቁሟል።

ይህ ሳምንታዊ ፌስቲቫል በርካታ ፋይዳዎች ያሉት ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል የሀገርን ታሪክና እሴት ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ፣ የጋራ መግባባትን መፍጠር፣ ቱሪዝምን እና ኢኮኖሚን ማሳደግ እንዲሁም በባህልና ቋንቋ ዘርፍ የሥራ ዕድል ፈጠራን ማበረታታት ይገኙበታል።

ዝግጅቱ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በአንድ መድረክ ተገናኝተው እውቀትና ልምድ የሚለዋወጡበት፣ የሰላም እና የመቻቻል እሴቶች የሚጎለብቱበት እንደሚሆን ይጠበቃል።





Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: