#FastMereja I ማርቭለስ ሪል እስቴት በሃይሌ ጋርመንት ሳይት ያስገነባቸውን የመኖሪያ ቤቶች የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ.ም ለደንበኞቹ ሊያስረክብ መሆኑን አስታወቀ። ተቋሙ በዛሬው እለት በዋና መሥሪያ ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የርክክብ መርሃ ግብሩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት እንደሚከናወን ገልጿል።
ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ በጥራትና በፍጥነት ግንባታቸውን በማጠናቀቅ የበርካታ ደንበኞቹን የቤት ባለቤትነት ህልም እውን ያደረገው ማርቭለስ ሪል እስቴት፣ ለሦስተኛ ጊዜ የሚያካሂደው ይህ የቤት ርክክብ የኩባንያውን ውጤታማነት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል። የተቋሙ ማርኬቲንግ ዋና ዳይሬክተር አቶ ረምዚ ሀሰን በመግለጫው ላይ እንደተናገሩት፣ ቤቶቹ ደረጃቸውን የጠበቁና ለዘመናዊ አኗኗር የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን አሟልተው የተገነቡ ናቸው።
ይህንን ታላቅ የርክክብ መርሃ ግብር በሁነት ዝግጅት ዘርፍ ልምድ ያለው “ሰሙ ኤቨንት እና ማርኬቲንግ” የሚያዘጋጀው ሲሆን፣ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ት ሰሚራ ወንድሙ ዝግጅቱ ዘመናዊነትንና ጥራትን አጣምሮ ለታዳሚዎች በሚያሳይ መልኩ እንደሚቀርብ አረጋግጠዋል። በሌላ በኩል፣ የሚዲያ ቅንጅት ሥራውን ላለፉት አስር ዓመታት በዘርፉ ስሙን ያገነነው “ቲኤች ሚድያ” በኃላፊነት እየመራው እንደሚገኝ ታውቋል።

Source: FastMereja









No comments yet.