#FastMereja I በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ ውስጥ ትናንት ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከአሶሳ ወደ ግልገል በለስ በመጓዝ ላይ በነበሩ ሲቪል መንገደኞች ላይ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ። ጥቃቱ የተፈጸመው መንገደኞቹ በማንኩሽ ከተማ አድረው ጉዟቸውን በጀመሩበት ወቅት መሆኑ ታውቋል።
እንደ ነዋሪዎች ምስክርነት፣ በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ30 እስከ 35 እንደሚደርስ የሚገመት ሲሆን፣ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶችም ሙሉ በሙሉ በቃጠሎ መውደማቸውን የሚያሳዩ ምስሎች በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ተሰራጭተዋል።
በአካባቢው ቀድሞውንም የታጣቂዎች እንቅስቃሴ እንደሚስተዋል የገለጹት የዓይን እማኞች፣ ድርጊቱን የፈጸመው ራሱን “የጉምዝ ነጻ አውጪ ኃይል” ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን መሆኑን ጠቁመዋል።
ጥቃቱ የተፈጸመበት ስፍራ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በሚገኝበት ወረዳ ውስጥ መሆኑ የጸጥታ ስጋቱን አሳሳቢ አድርጎታል። በጉዳዩ ላይ ከክልሉ መንግሥትም ሆነ ከመተከል ዞን የኮምዩንኬሽን መምሪያ በኩል ዝርዝር ማብራሪያ ለማግኘት የተደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም ሲል ዶቸ ቬለ ዘግቧል። ሆኖም የክልሉ ፖሊስ ባልደረባ ስለ ሁኔታው መረጃ ደርሷቸው ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን በወቅቱ ለዶቸ ቨለ በሰጡት ቃል አመልክተዋል።
Source: FastMereja








No comments yet.