#Ethiopia | ማዕቀቡ መነሳቱን የገለፀው በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአገር መከላከያ ንግድ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ነው።
ዳይሬክቶሬቱ፣ በኢትዮጵያ ላይ ይከተል የነበረውን የክልከላ ፖሊሲ በማንሳት አሁን ላይ በዓለም አቀፍ የጦር መሣሪያ ዝውውር ደንብ (ITAR) ቁጥጥር የሚደረግባቸውን እና ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዙ የፈቃድ ማመልከቻዎችን በየተራ እየገመገመ ነው።
ይህን ተከትሎ በቅርቡ በሚወጣ የደንብ ለውጥ፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የጦር መሳሪያ ዝውውር ደንብ – ITAR 126.1 ዝርዝር ውስጥ ከሚገኙ አገራት ተርታ “እንድትሰረዝ” የሚደረግ መሆኑን ጠቅሷል።
ይህ ደንብ በአሜሪካ ማዕቀብ ስር የሚገኙ የተወሰኑ አገራት፤
– ለመከላከያ ሠራዊት፣
– ለፖሊስ፣
– ለደህንነት እና ለሌሎችም የአገር ውስጥ የጸጥታ ኃይሎቻቸው የሚሆኑ የመከላከያ ቁሳቁሶችን እና አገልግሎቶችን ከውጭ ገዝተው ማስገባትም ሆነ ወደ ውጭ አገራት መላክ እንዳይችሉ የሚከለክል ነው።
ኢትዮጵያ በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ከነበረው የትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ ከኅዳር 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ከ4 ዓመታት በላይ በዚህ ማዕቀብ ውስጥ ቆይታለች።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #Tikvah #Diplomacy #GlobalNews #NewsUpdate
Source: GetuTemesgen









No comments yet.