የጀግናዋ አትሌት የብርጓል መለሰ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ነገ ይፈፀማልኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ የረጅም ርቀት ሩጫ መድረኮች በክብር…

- Advertisement -
Sidebar AD
የጀግናዋ አትሌት የብርጓል መለሰ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ነገ ይፈፀማል
ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ የረጅም ርቀት ሩጫ መድረኮች በክብር ስታስጠራ የቆየችው ጀግናዋ አትሌት የብርጓል መለሰ፣ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ነገ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚፈፀም ታውቋል።
ትላንትና በመደበኛ የልምምድ ወቅት ላይ እያለች በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ የሚታወስ ሲሆን፣ የቀብር ሥነ-ሥርዓቷም ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚከናወን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአትሌቷ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጾ፤ ለቤተሰቦቿ፣ ለወዳጅ ዘመዶቿ እንዲሁም ለመላው የስፖርት ቤተሰብ መፅናናትን ተመኝቷል።
Via የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: