በምዕራብ ሀረርጌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ጡሎ ወረዳ “ቀራ ፋርሾ” ተብሎ በሚጠራው ልዩ ቦታ ዛሬ ረፋድ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ።

​አደጋው የተከሰተው ከባጃጅ ጋር በተጋጨ የጭነት መኪና (ኮንቴይነር) ምክንያት መሆኑ ታውቋል። ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረው የጭነት መኪናው ከባጃጇ ጋር በፈጠረው ግጭት፣ በሰው ህይወት ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ በንብረት ላይም ከፍተኛ ውድመት መድረሱን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2