#ስደተኞችበየቀኑ 1,000 የሚደርሱ የደቡብ ሱዳን ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚሰደዱ ተመላከተ።ተመድ ባወጣው አዲስ ሪፖርት ከእነ…

- Advertisement -
Sidebar AD
#ስደተኞች
በየቀኑ 1,000 የሚደርሱ የደቡብ ሱዳን ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚሰደዱ ተመላከተ።
ተመድ ባወጣው አዲስ ሪፖርት ከእነዚህ ስደተኞች 95% የሚሆኑት ሴቶች እና ህፃናት መሆናቸውን ገልጿል።
የተመድ ስደተኞች ኤጀንሲ ቃል አቀባይ መሊሳ ፍሌሚንግ በጄኔቭ በሰጡት መግለጫ ወደኢትዮጵያ በሚሰደዱበት ወቅት ሴቶችም ሆኑ ወንዶች በግዳጅ ለጦርነት እንደሚመለመሉም ተናግረዋል።
በዚህም፣ ፍቃደኛ ያልሆኑ በመንገድ ላይ እያሉ በመልማይ ታጣቂዎች ኢላማ ተደርገው ግድያ እንደሚፈፀምባቸውም አብራርተዋል።
የተመድ የስደተኞች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከመጋቢት 2026 ጀምሮ ብቻ ከ100 ሺሕ የሚልቁ የደቡብ ሱዳን ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ተሰደው ገብተዋል።
Via.un news
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1