እንከባበር! – ኢራን

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ኢራን በኩዌት የታሰሩ ዜጎቿን በተመለከተ የአጸፋ እርምጃ የመውሰድ መብት እንዳለት አስታወቀች

በፋርስ ባሕረ ሰላጤ አቅራቢያ አራት ኢራናውያን በኩዌት የጸጥታ ኃይሎች መታሰራቸውን ተከትሎ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀገራቸው ተመጣጣኝ ምላሽ የመስጠት መብት እንዳላት አስታውቃለችል፡፡

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራቅቺ በሰጡት መግለጫ ኩዌት በሕገወጥ መንገድ በኢራን የባሕር ጓዝ ላይ ጥቃት መፈጸሟንና ዜጎቿን ማሰሯን ገልጸው የታሰሩት ግለሰቦች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡

በሌላ በኩል የኩዌት የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ በባሕር በኩል ወደ ሀገር ውስጥ ለመግባት ሲሞክሩ የተያዙት አራት ግለሰቦች የኢራን አብዮታዊ ዘበኛ አባላት መሆናቸውን እንዳመኑ ይፋ አድርጓል፡፡

ይህንን ድርጊት ተከትሎ ዮርዳኖስ የኩዌትን ሉዓላዊነት የሚጋፋ ተግባር ነው ስትል ድርጊቱን ያወገዘች ሲሆን ለኩዌት ያላትን ሙሉ ድጋፍ ገልጻለች፡፡

ኢራን ግን ግለሰቦቹ ከአብዮታዊ ዘበኛው ጋር ግንኙነት አላቸው መባሉን አስተባብላለች፡፡

#Iran #Kuwait #MiddleEast #Diplomacy #Jordan #RedSea #InternationalNews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1