ለረጅም ዘመናት በእንግሊዝ ሀገር የነበሩ ሦስት ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሱ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ከ158 ዓመታት በፊት በመቅደላ ጦርነት ወቅት ወደ በእንግሊዝ ሀገር የተወሰዱ ሦስት ታሪካዊ ቅርሶች በዛሬው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል። ቅርሶቹ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጓል።

በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕርፌሰር አበባው አያሌው እንደገለጹት፣ ወደ አገር የተመለሱት ቅርሶች የአፄ ቴዎድሮስ የወርቅ አምባር፣ የጸጉር ቆንዳላ ዘለላና መቅደላ ላይ ሕይወታቸው ባለፈበት ወቅት ለብሰውት የነበረው የሽማ ሸሚዝ ልብስ ቁራጭ ናቸው።

እነዚህ ቅርሶች በወቅቱ በእንግሊዝ ጦር አዝማችና በሌሎች ወታደሮች ተወስደው በሙዚየም የነበሩና አሁን ላይ በተደረገው ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ለኢትዮጵያ መመለሳቸውን ተናግረዋል።

ይህ ስኬት ለሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን በመጥቀስ፣ በሌሎች ሀገራት የሚገኙ ሌሎች የኢትዮጵያ ቅርሶችን ለማስመለስ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

ቅርሶቹን በመመለስ ሂደት ውስጥ አስተባባሪ የነበሩት አሉላ ፓንክረስት (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ቅርሶቹ ከ158 ዓመታት በፊት በመቅደላ ጦርነት ወቅት ወደ እንግሊዝ ተወስደው የነበሩና ከአፄ ቴዎድሮስ ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት ያላቸው መሆናቸውን ተናግረዋል።

በእንግሊዝ ሀገር ከሚገኘው የላንካስተር ኪንግስ ኦን ሬጅመንት ሙዚየም የተገኙ ሲሆን፣ አሁን ግን በስጦታ መልክ ለኢትዮጵያ እንዲመለሱ መደረጉን አሉላ ፓንክረስት (ዶ/ር) ገልጿል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#ጋዜጣ ፕላስ


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1