ምስጋና ኃይሉ ለኢትዮጵያ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኘች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በጋና አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ አትሌቶች ድንቅ ውጤት ማስመዝገባቸውን ቀጥለዋል።

በአትሌት አጃይባ አልዩ አማካኝነት የተገኘውን የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያ ተከትሎ፣ በዛሬው ዕለት በሴቶች የ800 ሜትር የፍጻሜ ውድድር አትሌት ምስጋና ኃይሉ ለሀገሯ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አበርክታለች።

በስታዲየሙ በተካሄደው አስገራሚ ፉክክር ምስጋና ከመጀመሪያው ዙር ጀምሮ የውድድሩን ፍጥነት በበላይነት ስትመራ የቆየች ሲሆን፣ በመጨረሻው ዙር ባሳየችው ከፍተኛ ብቃትና ፍጥነት ተቀናቃኞቿን ቀድማ በመግባት ድሏን አረጋግጣለች።

በተመሳሳይ ዜና በሴቶች የከፍታ ዝላይ የፍጻሜ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት በፀሎት አለማየሁ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት ሆናለች።

#አትሌቲክስ #አፍሪካሻምፒዮና #ምስጋናኃይሉ #በፀሎትአለማየሁ #ኢትዮጵያ #ስፖርት #ድል
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1