ለምሽት ብቻ 6 ሺህ ተሽከርካሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ መሆኑ ተገለጸ

- Advertisement -
Sidebar AD

ለምሽት ትራንስፖርት ብቻ ታክሲዎችን ጨምሮ አገልግሎት የሚሰጡ 6 ሺህ ተሽከርካሪዎችን በተመረጡና የሰው እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው አካባቢዎች ላይ በመመደብ በቀን ውስጥ 250 ሺህ የሚሆን ሰው እየተጓጓዘ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ለአሐዱ አስታውቋል።

ከተማዋ ለቱሪስትም ሆነ ለነዋሪዎች ምቹ እየሆነች መምጣቷን የገለፁት የቢሮው የህዝብ ትራንስፖርት ስምሪትና አደረጃጀት ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ ስዩም ናቸው።

ዳይሬክተሩ ከአሐዱ ሬዲዮ “ሁሉ ደህና” ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ አሁን ላይ በከተማዋ ከቀን በተጨማሪ የምሽት ትራንስፖርት ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

ይህም ከከተማዋ ማደግ ጋር ተያይዞ የኮሪደር ልማቱ በፈጠረው ምቹ ሁኔታ የማህበረሰቡን እንቅስቃሴ በምሽት ጭምር እንዲሆን በማድረጉ እንደሆነ አመላክተዋል።

ይህ ቁጥር በቂ አለመሆኑን ያነሱት ዳይሬክተሩ ይህንን በማስፋት የከተማዋን ትራንስፖርት የማሳለጥ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

#አሐዱ


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1