አዲስ አበባ የአፍሪካ ንግድ ትምህርት ቤቶች ማኅበር ዓመታዊ ጉባኤን እያስተናገደች ትገኛለች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የ2026 የአፍሪካ ንግድ ትምህርት ቤቶች ማኅበር ወይም በምህፃረ ቃሉ (AABS) ዓመታዊ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

በክቡር ኮሌጅ አዘጋጅነት በኢትዮጵያ የ2026 የአፍሪካ ንግድ ትምህርት ቤቶች ማኅበር (AABS) አመታዊ ኮንፈረንስ በዛሬው እለት “የንግድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ያላቸው ሚና“ በሚል መሪ ቃል በተባበሩት መንግሥታት ኢኮኖሚ ኮሚሲዬን አፍሪካ ስብሰባ አዳራሽ መካሄድ ጀምሯል።

ለኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፍ እና በአፍሪካ የትምህርት ደረጃ እያደገ ላለው ትልቅ ምዕራፍ፣ የ2026 የአፍሪካ ንግድ ትምህርት ቤቶች ማኅበር (AABS) ዓመታዊ ኮንፈረንስ እንድታዘጋጅ ኢትዮጵያ መመረጧ የሚታወስ ነው።

በዚህም ኮንፍረንስ ከ150 በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ዳይሬክተሮች እና የአለም አቀፍ አካዳሚክ መሪዎች ከመላው አፍሪካ እና ከዓለም አቀፍ ተሳትፈዋል።

ክቡር ኮሌጅ በኢትዮጵያ እያደገ ያለው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም እንደ አስተናጋጅ ተቋም ይህንን ትልቅ ጉባኤ በማዘጋጀት ግንባር ቀደም ሆኖ አዘጋጅቷል።

የክቡር ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ደሳለኝ መኩሪያ ኮሌጁ ከሀገራዊ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች እና አህጉራዊ ግቦች ጋር ተጣጥሞ አግባብነትና ተፅዕኖ ያለው ስራ ፈጣሪ ትምህርት ለመስጠት ቁርጠኛ መሆኑን ማሳያ እንደሆነ ገልጸዋል።

በተጨማሪም የኮንፈረንሱ ዋና አላማ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ/አለም አቀፍ ተቋማት መካከል የእውቀት ሽግግር እንዲኖር ለማስቻል ፣ በሃገራችን የኮንፍረስ ቱሪዝም ተጠቃሚነትን በማሳደግ ለዓለም በጎ ገፅታዋን ለማሳደግ እንደሆነም ተነግሯል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም ኮንፍረንሱ በምርምር ፣በፈጠራ ፣በፋኩልቲ ልማት እና በስራ ፈጠራ ውስጥ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማምጣት፤የኢትዮጵያን የንግድ ተቋማት ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በጋራ የሚሰሩበትን በጎ አጋጣሚ ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል::

ኮንፍረንሱ እስከ ነገ ድረስ የሚቆይ ሲሆን ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በትብብር የተዘጋጀ እንደሆነ ተጠቁሟል ።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu #ጌጡ






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1