ኢትዮጵያ እና ጣሊያን ለቀበና ወንዝ ልማት ፕሮጀክት የሚውል የ5 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ስምምነት ተፈራረሙየኢትዮጵያ እና የጣሊያ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ኢትዮጵያ እና ጣሊያን ለቀበና ወንዝ ልማት ፕሮጀክት የሚውል የ5 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ስምምነት ተፈራረሙ
የኢትዮጵያ እና የጣሊያን መንግሥታት በየካ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን የቀበና ወንዝ ተፋሰስ ለማልማት የሚያስችል የ5 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት ዛሬ ተፈራርመዋል።
ይህ በ24 ወራት ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት ይበቃል ተብሎ የሚጠበቀው “የከበና ወንዝ ገባር ወንዞች ልማት ፕሮጀክት” በአዲስ አበባ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ አማካኝነት ተግባራዊ እንደሚደረግ ተጠቁሟል።
ፕሮጀክቱ በዋናነት የአካባቢ ጥበቃን፣ የከተማን የአየር ንብረት የመቋቋም አቅምን ማሳደግ እና የከተማዋን ውበት መጠበቅ ላይ ትኩረት ያደርጋል።
በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እንደገለጹት፤ ፕሮጀክቱ የወንዝ ዳርቻዎችን በጂኦ-ኢንጂነሪንግ ዘዴ ከመጠበቅ ባለፈ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችን በመገንባት የወንዙን መበከል ለመከላከልና ለአካባቢው ማህበረሰብ ምቹ የመዝናኛ ስፍራዎችን ለመፍጠር ያለመ ነው።
ይህ ፕሮጀክት በወንዝ ዳርቻው የሚኖሩ 9 ሺህ ገደማ ነዋሪዎችን በቀጥታ ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን፣ በተለይም ሴቶች በጽዳት እና በመዝናኛ አገልግሎት አስተዳደር ዘርፍ ወደ ስራ እንዲሰማሩ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2