የኢትዮጵያ አየር መንገድ ልዩ የአየር ላይ ትርኢት በማቅረብ ላይ ይገኛል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተመሰረተበትን 80ኛ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ የአውሮፕላኖች ትርኢት እያከናወነ ነው።

በዓይነቱ ለየት ያለውንና አውሮፕላኖች ለሕዝብ እይታ የቀረቡበትን ይህንን መርሐ ግብር የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) እንዲሁም የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በይፋ አስጀምረውታል።

ይህ ዝግጅት አየር መንገዱ ስምንተኛ አስርት ዓመታትን ያስቆጠረበትን ታሪካዊ ጉዞ ከደንበኞቹና ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በጋራ ለማክበር ያለመ መሆኑን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

አየር መንገዱ ባለፉት 80 ዓመታት ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀምና የአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት መሪ በመሆን አህጉራትንና ሀገራትን በማስተሳሰር በዓለም አቀፍ የንግድና የባህል ልውውጥ ውስጥ ጉልህ ድርሻ ሲወጣ ቆይቷል።

#EthiopianAirlines #Aviation #Anniversary #80YearsOfExcellence #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2