የ15 ሺህ ዶላር የቪዛ ማስያዣው ቀረ
የቀጣዩን የዓለም ዋንጫ ትኬት ለገዙ ተመልካቾች የአሜሪካ መንግሥት ልዩ እፎይታ የሚሰጥ ውሳኔ አስተላለፈ።
ቀደም ሲል የቪዛ ቆይታ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉ ሰዎችን ለመቀነስ በሚል ተጥሎ የነበረው የ15,000 ዶላር (ከ850,000 ብር በላይ) የቪዛ ማስያዣ ክፍያ፣ ትኬት በገዙ የ50 አገራት ዜጎች ላይ ተፈጻሚ እንደማይሆን የትራምፕ አስተዳደር በይፋ አስታውቋል።
ይህ ውሳኔ በተለይ ለአምስቱ የአፍሪካ አገራት (አልጄርያ፣ ኬፕ ቨርዴ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ሴኔጋል እና ቱኒዝያ) ደጋፊዎች ትልቅ እድል የፈጠረ ሲሆን፣ ተጫዋቾችና አሠልጣኞችም ከዚህ ቀደም ከክፍያው ነፃ መደረጋቸው ይታወሳል።
ይሁን እንጂ እንደ ኢራን እና ሔይቲ ያሉ አገራት ደጋፊዎች አሁንም በውሳኔው ውስጥ ያልተካተቱ ሲሆን፣ ቱሪስቶች የአምስት ዓመት የማኅበራዊ ሚዲያ ታሪካቸውን እንዲያቀርቡ የሚጠይቀው ደንብ እንደጸና ይገኛል።
ፊፋ ከዋይት ሀውስ ጋር በመተባበር ስኬታማ ውድድር ለማካሄድ እየሰራ መሆኑን ገልጾ፣ የአሜሪካ መንግሥት ላሳየው ትብብር ምስጋናውን አቅርቧል።
አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በጋራ በሚያስተናግዱት በዚህ ታላቅ ስፖርታዊ ኩነት ላይ ተመልካቾች የቪዛ ቆይታቸውን አክብረው ከወጡ ያስያዙት ገንዘብ (ክፍያው በሚመለከታቸው ላይ) ተመላሽ እንደሚደረግላቸው ተገልጿል።
@seledadotio

No comments yet.