#Ethiopia | በበርካታ ዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ስታደርግ የቆየችው ዝነኛዋ አትሌት ሻምበል ባሻ የብርጓል መለሰ የቀብር ሥነ ሥርዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በክብር ተፈጽሟል።
በመጋቢት ወር 1982 ዓ.ም በሰሜን ወሎ መቄት ወረዳ የተወለደችው አትሌቷ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሩጫው ዓለም በመግባት ስኬታማ ጉዞ ስታደርግ ቆይታለች።
በ2003 ዓ.ም የመከላከያ መቻል ስፖርት ክለብን በመቀላቀል በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ በ10 ኪሎ ሜትር፣ በሀገር አቋራጭ እንዲሁም በማራቶን ውድድሮች በርካታ ድሎችን ለሀገሯና ለክለቧ አስመዝግባለች።
አትሌት የብርጓል መለሰ እ.ኤ.አ በ2015 በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የነሐስ ሜዳሊያ፣ በ2013 በዓለም ሀገር አቋራጭ ውድድር የብር ሜዳሊያ እንዲሁም በሂውስተን፣ በሻንጋይ፣ በፕራግ እና በሊዝበን ማራቶኖች አንደኛ በመውጣት ታላቅ ውጤት ያስመዘገበች ጀግና ነበረች።
አትሌቷ በካናዳ ለሚካሄደው የኦታዋ ማራቶን ዝግጅት እያደረገች በነበረበት ወቅት በደረሰባት ድንገተኛ የጤና እክል ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።
በዛሬው የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች፣ የጦር ኃይሎች መኮንኖች፣ አትሌቶችና ቤተሰቦቿ በተገኙበት በመከላከያ የክብር ዘብ የታጀበ ሽኝት ተደርጎላታል።
አትሌት የብርጓል በትዳር አጋሯ አትሌት ወሰን ዘለቀና በሁለት ሕፃናት ልጆቿ እንዲሁም በሥራ ባልደረቦቿ ዘንድ በትሕትናዋና በአርአያነቷ የምትታወስ ታላቅ ስፖርተኛ ነበረች።
Getu Temesgen ( ጌጡ ተመስገን) ሚዲያና ኮሙኒኬሽንስ በጀግናዋ አትሌት ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን ለቤተሰቦ፤ ለአድናቂዎቿ መጽናናትን እንመኛለን።
#athletics #ethiopianathletes #yebrgualmelese #sportnews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen








No comments yet.