#Ethiopia | የዩኒቨርሲቲ አመራሮች ምደባ ከብሔር ስብጥር አሰራር ወጥቶ፣ በሀገር አቀፍ የውድድር ማስታወቂያ፣ በእውቀትና በችሎታ ላይ ብቻ እንዲመሰረት እየተደረገ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ ለማድረግና የጥናትና ምርምር ማዕከልነታቸውን ለማረጋገጥ የታለመ አዲስ አቅጣጫ ተቀምጧል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ጋር ባደረጉት ውይይት እንደገለጹት፤ ዩኒቨርሲቲዎች በዘር የሚሰባሰቡባቸው ሳይሆኑ፣ በነፃነት የሚያስቡና በብቃት የሚመሩ ተቋማት እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ ነው።
ይኸውም በቀጣይ የዩኒቨርሲቲ አመራሮች ሹመት በግልጽ የውድድር ማስታወቂያ በእውቀትና በችሎታ ብቻ ይሆናል ብለዋል።
ተቋማቱ ከማንኛውም የፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ ሆነው የጥናትና ምርምር ማዕከል እንዲሆኑ ይደረጋል ሲሉም መናገራቹውን ትርታ ከትምህርት ሚኒስቴር ሰምቷል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #TirtaRadio
#UniversityLeadership #የዩኒቨርሲቲአመራር #HigherEducation
Source: GetuTemesgen








No comments yet.