#Ethiopia | በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፈው “የመደመር መንግሥት“ መጽሐፍ የዓረብኛ ትርጉም የምረቃ ሰነ-ስርዓት በአቡዳቢ ተካሄዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሻክቦት ናሃያን አል ናሃያን እና ሌሎች የአገሪቷ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ንጉሣዊ ቤተሰቦች፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ የቢዝነስ ማህበረሰቡ፣ እና የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ አባላት ታዳሚ ሆነዋል።
በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት ”የመደመር እሳቤ” ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሃገራትና ለዓለም ህዝቦች ያላትን የትብብር መርህ የሚያሳይ መሆኑን ገልፀዉ ወደ አረብኛ መተርጎሙ በመደመር እሳቤ የምትመራዋን ኢትዮጵያን በመካከለኛው ምሥራቅ ለሚገኙ ሁሉም ዓረብኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሀገራትና ሕዝቦች ለማስተዋወቅ እንደሚያግዝ ገልጸዋል።
አክለዉም የኢትዮጵያ እና የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የሁለትዮሽ ግንኙነት በጠንካራ የወንድማማችነት መርህ ላይ የተመሰረተ መሆኑንም አንስተዋል።
የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሻክቦት ናሃያን አል ናሃያን በበኩላቸው ”የመደመር መንግስት” መጽሀፍ በዐረብኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በመቅረቡ የተሰማቸውን ደስታ በመግለፅ መፅሀፋ በህዝቦች መካከል ያለውን የባህልና የእሴት ትስስር እንደሚያሳድግ ተናግረዋል።
በተጨማሪም በሃገራቸው እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ጠንካራ ግንኙነት በአስቸጋሪ ጊዚያት ማይናወጥ መሆኑን በማንሳት ግንኙነቱን የበለጠ አጠናክሮ ለማስቀጠል ሃገራቸው ቁርጠኛ መሆኗን ገልፀዋል።
በፕሮግራሙ ላይ በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቆንስል ጄኔራል አቶ ዘሪሁን መገርሳን ጨምሮ የዕለቱ የክብር እንግዶች መፀሀፉን በይፋ የመረቁ ሲሆን የኢትዮጵያን የባህላዊ ምግቦችና ዉዝዋዜዎች ለዕይታ መቅረባቸዉን በአቡዳቢ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #AMN


Source: GetuTemesgen








No comments yet.