ኢቦላ በኮንጎ ዳግም ተቀሰቀሰ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል በኢቦላ ወረርሽኝ ሳቢያ 65 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ኢቦላ በኮንጎ ዳግም ተቀሰቀሰ
በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል በኢቦላ ወረርሽኝ ሳቢያ 65 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን የአፍሪካ በሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታወቀ።
ኢቱሪ በተባለው የአገሪቱ ክፍል ወረርሽኙ መቀስቀሱን ማዕከሉ ገልጿል።
በዚህ ሳቢያም ወደ 246 ሰዎች በወረርሽኙ መያዛቸውን ሲገልጽ 65 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል ብሏል።
አብዛኛዎቹ ሟቾች ወርቅ በሚወጣባቸው ሞንግዋሉ እና ርዋምፓራ በተሰኙ መለስተኛ ከተሞች የተገኙ መሆኑንን የቢቢሲ ዘገባ ያመላክታል።
አሁን ላይም ከኮንጎ፣ ርዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን እና ከሌሎች ዓለም አቀፍ አጋር አካላት ጋር በጉዳዩ ላይ ልመክር ነው ብሏል።
በፈረንጆቹ 1976 የተገኘው ኢቦላ በአገሪቱ ሲከሰት የአሁኑ ለ17ኛ ጊዜ መሆኑን ዘገባው አስታውሷል።
ቫይረሱ በሰውነት ንክኪ እንዲሁም በተጎዳ ቆዳ በሚገባ የሰውነት ፈሳሽ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍና አደገኛ ገዳይ መሆኑ ይነገራል።
እስካሁን ክትባት አልተገኘለትም በሚባለው በዚህ ቫይረስ የተያዘ ሰው የመሞት እድሉ 50 በመቶ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያመላክታል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1