የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 3,600 የውጪ ሃገር ዜጎች በሀሰት የኢትዮጵያ ፓስፖርት ለመያዝ ሲንቀሳቀ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 3,600 የውጪ ሃገር ዜጎች በሀሰት የኢትዮጵያ ፓስፖርት ለመያዝ ሲንቀሳቀሱ ደርሼባቸዋለሁ ብሏል።
አገልግሎቱ ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች ሀሰተኛ የልደት ሰርተፍኬት፣ መታወቂያ እና ፋይዳ በመያዝ ህጋዊ አገልግሎት ለማግኘት ሲሉ  እንደተደረሰባቸው ተናግሯል።
በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የፓስፖርት አገልግሎት ዳሬክተር የሆኑት አቶ ሙሉጌታ ብርሃኑ ከድንበር አከባቢ የሚመጡ ኢትዮጵያውያን ከውጪ ሃገር ከሚመጡ ዜጎች ጋር የሚመሳሰል ማንነት ስላላቸው የውጪ ዜጎች ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ሃሰተኛ ሰነድ ለመያዝ ሙከራ እንደሚያደርጉ አስረድተዋል።
አቶ ሙሉጌታ ረጅም ዓመታትን በኢትዮጵያ የኖሩ ኤርትራዊያን የኢትዮጵያ ዜግነት ሊያገኙ የሚችሉበትን ሁኔታም አስረድተዋል።
በሪፈረንደሙ ወቅት ያልመረጡ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ የዜግነት መብት ይሰጣቸዋል፣ ሪፈረንደም የመረጡ ግን ህጉን ተከትለው የዜግነት ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ ብለዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የሚነሱበትን ቅሬታዎች ለመፍታት እየሰራ መሆኑን ያነሱት ኃላፊው ፣ ሰዎችም ለአግልግሎት ሲመጡ የሚያጋጥማቸውን እንግልት ለመቀነስ የሚጠበቅባቸውን ሰነድ ሁሉ አሟልተው እንዲመጡ አሳስበዋል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: