“ሥላሴ” የሚለው ቃል “ሠለሰ” ሦስት አደረገ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ሦስትነት ማለት ነው፡፡

- Advertisement -
Sidebar AD

ቅድስት ሥላሴ ስንል ለሥላሴ ቅድስት ብለን እንቀጽላለን፡፡ ቅድስት ሥላሴ ማለት ልዩ ሦስትነት ማለት ነው፡፡ ይህም ሦስት ሲሆኑ አንድ፣ አንድ ሲሆን ሦስት ስለሚሆኑ ልዩ ሦስትነት ተብሏል፡፡ ሥላሴ የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ያለና የሚኖረውን አምላክ ለመግለጽ የተጠቀመው የአንጾኪያው ቅዱስ ቴዎፍሎስ በ169 ዓ.ም ነው፡፡ በኒቅያ ጉባዔም 318ቱ ሊቃውንት አጽንተውታል፡፡ ሊቃውንቱ በቅዱሳት መጻሕፍት የተመሰከረውን የእግዚአብሔርን ፍጹም አንድነትና ልዩ ሦስትነት ለእኛ በሚረዳ ቋንቋ ገለጡት እንጂ አዲስ ትምህርት አላመጡም፡፡ ምስጢረ ሥላሴ ማለት የአንድነት የሦስትነት ምስጢር ማለት ነው፡፡ ምሥጢር መባሉም በእምነት የተገለጠ፣ ያለ እምነትም የማይመረመር ስለሆነ ነው፡፡

ይኸውም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት ሲሆኑ በባሕርይ በሕልውና፣ በመለኮት ደግሞ አንድ ናቸው፡፡ እንደዚህ ባለ ድንቅ ነገር አንድ ሲሆኑ ሦስት፣ ሦስት ሲሆኑ አንድ ይባላሉና፣ ይህም ልዩ ሦስትነት ረቂቅ እና በሰው አእምሮ የማይመረመር ስለሆነ ምስጢር ይባላል፡፡ ስለዚህም አንድ አምላክ፣ ሦስቱ አካላት ብለን እናምናለን፡፡ ሥላሴ ሦስት ናቸው ስንል እንደ አብርሃም፣ እንደ ይስሐቅ እንደ ያዕቆብ የተነጣጠለና በክብርም ሆነ በዘመን የሚበላለጥ የሚቀዳደም ማለታችን አይደለም፡፡ ሦስት ሲሆኑ አንድ ናቸው እንጂ፡፡ አንድ ናቸውም ስንል ከሰው ሁሉ ቀዳሚ ሆኖ እንደተፈጠረው እንደ አዳም ሦስትነትን የሚጠቀልል መቀላቀል ማለታችን አይደለም፡፡ አንድ ሲሆኑ ሦስት ናቸው እንጂ እንዲል ቅዳሴ ማርያም፡፡

የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በሰው ምሳሌ ይገለጻል፡፡ ሰው በነፍሱ ሦስትነት አለው፡፡ ይኸውም ልብነት፣ ቃልነት፣ ሕይወትነት ነው፡፡ በልብነቷ አብ፣ በቃልነቷ ወልድ፣ በሕይወትነቷ መንፈስ ቅዱስ ይመስላሉ፡፡ የነፍስ ልብነቷ፣ ቃልነቷን፣ ሕይወትነቷን ከራሷ ታስገኛለችና፡፡ ቃልና ሕይወት ከአንዷ ልብ ስለተገኙ በከዊን ወይም በመሆን ልዩ እንደሆኑ በመናገርም ይለያሉ፡፡ እንዲሁም አብ ወልድን በቃል አምሳል ወለደው፣ መንፈስ ቅዱስንም በእስትንፋስ አንጻር አሰረጸው፡፡ ነፍስ ስትገኝ በሦስትነቷ በአንድ ጊዜ ተገኘች አንዷ ልብነቷ ቀድሞ ቃልነቷና እስትንፋስነቷ በኋላ አልተገኙም፡፡ ሥላሴም አንዱ ከአንዱ ሳይቀድሙ ተገኝተዋልና፡፡ ይህን ምስጢረ ሥላሴ የተረዱ ገዳማውያን አንድነቱንና ሦስትነቱን አምነው ያመልኩታል፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: