የትግራይ ክልል አስተዳደርን ተቆጣጥሬያለሁ ያለው የህወሓት አስተዳደር በሳዑዲ ዓረቢያ ሞትን ለሚጠባበቁ ስደተኞች ምህረት እንዲደ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የትግራይ ክልል አስተዳደርን ተቆጣጥሬያለሁ ያለው የህወሓት አስተዳደር በሳዑዲ ዓረቢያ ሞትን ለሚጠባበቁ ስደተኞች ምህረት እንዲደረግ ጠየቀ
ህወሓት የሚመራው እና የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንትነትን ተረክቤያለሁ ያለው ኃይል በጽሕፈት ቤቱ በኩል ለሳዑዲ ዓረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሃን አል ሳዑድ በላከው ደብዳቤ በሞት አደጋ ላይ ለሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጅ ስደተኞች አስቸኳይ የሰብአዊ ምህረት ጥያቄ አቀረበ።
 
በዚህም ላይ ስደተኞች በከፍተኛ ሁኔታ ረሃብ እና የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በመፍራት የሸሹ በመሆናቸው ምህረትን ጠይቋል።
ምንም እንኳ ስልጣን ተረክቤያለሁ ያለው ኃይል ከፌደራል እውቅና ባይኖረውም ከክልሉ አስተዳደር ከዚህ ቀደም የሚወጡ ደብዳቤዎች የጊዜያዊ አስተዳደር የሚል ቃላትን የሚጠቀሙ ሲሆን አሁን የቀድሞውን ምክር ቤት የመለሰው ህወሓት የትግራይ ክልላዊ መንግሥት የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት በሚል የወጣ ነው።
በፕሬዝዳንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ተፈርሞ በወጣው ደብዳቤ ላይ እንደተመለከተው ስደተኞቹ ወንጀለኞች ሳይሆኑ በጦርነትና በሰው ሰራሽ ረሃብ ምክንያት ለህልውናቸው ሲሉ የተሰደዱ ንጹሃን ናቸው፡፡
የምህረት ጥያቄ ያቀረቡት ደብረጽዮን በሞት አደጋ ላይ የሚገኙ ስደተኞች ላይ ሊወሰድ የታሰበ ማንኛውም የቅጣት እርምጃ እንዲቆምና ምህረት እንዲደረግላቸው ጥሪ አቅርበዋል። አክለውም ደህንነቱ የተጠበቀ መመለስ እንዲደረግላቸውም በመጠየቅ ስደተኞቹ ከጥቃት ተጠብቀው ወደ ትግራይ የሚመለሱበት ሁኔታ ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ ድርጅቶች ጋር በመተባበር እንዲመቻች ጥሪ አቅርቧል።
ደብዳቤው አክሎም ሀሉም አካላት የሞራል ግደታ አለበት ያለ ሲሆን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብና የሳዑዲ መንግሥት ተጋላጭ የሆኑ ዜጎችን የመጠበቅ የጋራ የሞራል ግዴታ እንዳለባቸው አንስቷል። የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ያለውን የፍትህ እና የምህረት ባህል በመጥቀስ ሊቀለበስ የማይችል ሰብአዊ ጥፋት እንዳይከሰት ፈጣን እርምጃ ይወሰዳል የሚል እምነት እንዳለው ገልጿል ።
 
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1