‹‹የአዲስአበባ አመታዊ በጀት 350 ቢሊዮን ብር ቢሆንም፤ ለወንዝ ዳር ፕሮጄክት ብቻ 1.3 ትሪሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል.››

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ከሰሞኑ በተዘጋጀ አንድ የውይይት መድረክ ላይ የአዲስአበባን የኮሪደር እና የወንዝ ዳር ፕሮጄክቶችን በተመለከተ አነጋጋሪ ጉዳይ ተሰምቷል፡፡ ናሽናል ሚዲያ አክሲዮን ማህበር “አዲሲቷ አዲስ” በሚል መሪ ቃል የአዲስ አበባ ከተማን የማደስ እና የልማት ስራዎች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ትላንት በዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም አካሂዶ ነበር፡፡

በዚህ መድረክ ላይ የተሳተፉ አካላት በልማቱ ሂደት ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎችን ሰንዝረዋል። አንድ ተሳታፊ ከተማዋን ለማደስ የተሰራው የፋይናንስ ሞዴል እና ምንጩ ምን እንደሆነ ጥያቄ አቅርበዋል። ለዚህ ጥያቄ የኢዜማ ፓርቲ አመራር እና የአዲስአበባ ከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ ሰይፉ አነጋጋሪ ምላሽን ሰጥተዋል፡፡

አቶ ግርማ፣ ‹‹የአዲስ አበባ በጀት 350 ቢሊዮን ብር ሆኖ፤ በኮሪደር ልማቱ ግን በወንዝ ዳር ብቻ 1.3 ትሪሊዮን ብር ፈሰስ ተደርጎበታል›› ሲሉ አነጋጋሪ ምላሽን ሰጥተዋል። የኮሪደር ልማት የፋይናንስ ፕላን ምን ይመስል እንደነበር ሲያስረዱም፣ ‹‹ኮሪደሩ ከመንግስት ካዝና እንደሚሰራ ተደርጎ›› መወሰዱ ልክ አይደለም ይላሉ። ‹‹የፋይናንስ ፕላኑ የወጣው በአብዛኛው በግሉ ሴክተር እንዲሰራ ተደርጎ ነው። የመንግስት ትልቁ ሚና በተለይ መሰረተ ልማቶቹ የሚቀናጁበትን ሁኔታ ነበር›› ሲሉ ገልጸዋል።

‹‹ለምሳሌ በመንግስትና በግል አጋርነት በወንዝ ዳር ብቻ በሰራናቸው ስራዎች ከ1.3 ትሪሊዮን ብር በላይ ወጭ ተደርጓል›› ነው ያሉት አቶ ግርማ። ለልማት ግንባታ ገንዘቡ ከየት መጣ? የሚለውን ጥያቄ በተመለከተ “የህብረተሰቡ በተለይ የባለሃብቱ ተሳትፎ በጣም ትልቅ ድርሻ ነበረው” ብለዋል ሲል አንድ አፍታ ዘግቧል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1