ማርቨለስ ሪል እስቴት በኃይሌ ጋርመንት የገነባቸውን መኖርያ ቤቶች ለደንበኞች አስረከበ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ማርቨለስ ሪል እስቴት በኃይሌ ጋርመንት መስቀለኛ መንገድ አካባቢ የገነባቸውን መኖሪያ ቤቶች ለደንበኞቹ አስረክቧል።

ኩባንያው ቤቶቹን ያስረከበው “የግንባታ መጓተት” ታሪክን ለመቀየር በገባው ቃል መሠረት ሲሆን፣ ይህ ፕሮጀክት ድርጅቱ ቤቶችን ለደንበኞች ያስረከበበት ለ3ኛ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

በምረቃና የቁልፍ ማረከቢያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የዘርፉ ባለሙያዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የማርቨለስ ሪል እስቴት ማርኬቲንግ ዋና ዳይሬክተር አቶ ረምዚ ሀሰን በወቅቱ እንደገለጹት ኩባንያው በጥራትና በጊዜ አጠቃቀም ረገድ የሚታየውን ክፍተት ለመሙላት በቁርጠኝነት እየሠራ ይገኛል።

አክለውም ቤቶቹ ከሽያጭ ባሻገር “ሁሉንም በአንድ ጣሪያ ሥር” በሚል የአገልግሎት ዘይቤ በራሱ ባለሙያዎች የንብረት አስተዳደር፣ የዘመናዊ ጥገናና የጥበቃ አገልግሎት እንደሚቀርብላቸው ጠቁመዋል።

ሪል እስቴቱ በዚህ ዙር ያስረከባቸው 48 ቤቶች በሙሉ ባለ 3 መኝታ ክፍሎች ሲሆኑ፣ እንደ ደንበኞቹ ፍላጎት በከፊል (Semi-finished) እና ሙሉ በሙሉ (Fully-finished) ተጠናቀው የቀረቡ ናቸው።

ተቋሙ ከዚህ ቀደም ከ40 በላይ ባለ ሁለት መኝታ ቤቶችን ማስተላለፉ ይታወሳል።

አካባቢው ለትራንስፖርት ምቹ፣ በመንግሥት ትኩረት ተሰጥቶት እየለማ ያለ፣ እንዲሁም የመጫወቻ ሥፍራዎች፣ ሆስፒታሎችና ትምህርት ቤቶች በቅርበት የተሟሉለት በመሆኑ ስትራቴጂያዊ ምርጫ መሆኑ ተነግሯል።

ማርቨለስ ሪል እስቴትእስካሁን ያከናወናቸውን ፕሮጀክቶች በሙሉ ያለ ምንም የጊዜ መዘግየት ማጠናቀቁን የገለጸ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅትም በዚሁ በኃይሌ ጋርመንት አካባቢ የሌሎች ተጨማሪ 4 ሳይቶችን ግንባታ በከፍተኛ ፍጥነት እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu #ጌጡ






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2