#Ethiopia | ከፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕን ተከትሎ ወደ ቻይና የቀናው ከፍተኛ የአሜሪካ ልኡክ ወደ አገሩ ከመመለሱ በፊት በስጦታ መልክ የተቀበለውን በሙሉ እዛው ቻይና ጥሎ መሄዱ ታውቋል።
በረቀቀው የስለላ አለም ለቡድኑ አባላት የተሰጡት የተለያዩ ከፍተኛ ግምት እና ዋጋ ያላቸው ስጦታዎች በውስጣቸው ድብቅ የኤሌክትሮኒክ እና ሳይበር መጥለፊያ ሊኖራቸው እንደሚችል በመሰጋቱ ነው እንዲጣሉ የተደረገው።
ስለጉዳዩ እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚገልፁት የልኡክ አባላት ከትልልቅ ስጦታዎች ባሻገር እንደ ጊዜያዊ መታወቂ/ ባጅ የመሰሉ ጥቃቅን ነገሮች ሳይቀር ፕሬዝደንቱ በሚጓጓዙበት ወደ ኤርፎርስ ዋን አውሮፕላን ከመሳፈራቸው በፊት ወደ ቆሻሻ ገንዳ እንዲጥሉ መደረጉ ነው የተገለፀው።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#ቅዳሜገበያ
#etbusinessview#kidamegebeya#trump #ኤርፎርስ_ዋን #airforce_one
Source: GetuTemesgen









No comments yet.