ተከሳሽ ምስጋና ሙሉጌታ የስርቆት ወንጀሉን የፈፀመችው በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ቦታው ካራ ቆሬ መብራት ኃይል ጀርባ ከሚገኝ አንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ነው።
ግለሰቧ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ስትሰራ ከነበረችበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ለ ሦስት ሳምንታት ስትሰራ ቆይታለች፡፡
አሰሪዎቿ ወደ ስራ በሄዱበት አጋጣሚ ግምታቸው 267ሺህ 340 ብር የሚያወጡ የተለያዩ የአዋቂና የህፃናት አልባሳትን፣ ታብሌት ስልክ፣ የጆሮና የጣት የወርቅ ጌጣጌጥ፣ የብር ሃብል፣ የእጅ ሰዓትና 3 ሺህ 500 ብር ሠርቃ ትሰወራለች፡፡
ተከሳሿ በወቅቱ ስትቀጠር በቂ ተያዥ ባታቀርብም ፖሊስ ባደረገው ክትትል ግለሰቧ ከነበረችበት ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠምባሮ ልዩ ወረዳ ከእነ ንብረቱ እንተያዘች በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የካራ አካበቢ ፖሊስ ጣቢያ አስታውቋል።
ፖሊስ በግለሰቧ ላይ አስፈላጊውን ምርመራ በማጣራት አቃቤ ህግ ክስ መስርቶባት ጉዳዩን የተመለከተው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ቀራንዮ ምድብ የወንጀል ችሎት ተከሳሽ ምስጋና ሙሉጌታ ጥፈተኛነቷን በማረጋገጡ በ5 አመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ ወስኗል፡፡
ህብረተሰቡ የቤት ሰራተኛ ሲቀጥር በቂ ተያዥና ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ እንዳለባቸው እና ወንጀል ተፈፅሞ ሲገኝም በወቅቱ ለፖሊስ ማሳወቅ እንደሚገባም መልዕክቱን አስተላልፏል።
Addis Ababa police

Source: Yeneta Tube









No comments yet.