ለሀገር ህልውና አስጊ የሆነውን የምሁራን ልዩነት ለማስታረቅ እንደሚሰራ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ገለጸ

- Advertisement -
Sidebar AD

የተከፋፈለውን የምሁራን አመለካከት ወደ አንድ ሀገራዊ እሳቤ በማምጣት ለማስታረቅ እንደሚሰራ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ ለአሐዱ አስታውቋል።

የሀገሪቱን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ እና የህዝብን ሰላም የሚያናጉ “ጽንፈኛ” እሳቤዎች መታረቅ እንዳለባቸው ፓርቲያቸው በጽኑ እንደሚያምን የገለጹት የፖርቲው ፕሬዝዳንት አቶ አብርሃም ጌጡ ናቸው።

ፕሬዝዳንቱ ከ”አሐዱ መድረክ” ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የተከፋፈለ የምሁራን ሀሳብ ለሀገሪቱ ቀውስ መፈጠሩን አንስተው፣ ፓርቲያቸው ይህንን ክፍተት ለማስተካከል ሲሰራ መቆየቱን አክለዋል።

በሰዎች መካከል የተለያየ አመለካከት መኖሩ ተፈጥሯዊ መሆኑን ያነሱት አቶ አብርሃም፤ ነገር ግን ወደ ግጭት፣ ጦርነት እንዲሁም ሀገርና ህዝብን ወደ ከፋ ችግር የሚወስዱ አስተሳሰቦች መታረቅ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

ፓርቲያቸው በሚያደርገው ሰላማዊ ትግል ወደ ሁከት የሚያመሩ የምሁራን እሳቤዎችን ወደ መግባባት ማምጣት ዋነኛው ትኩረቱ መሆኑንም አብራርተዋል።

በመሆኑም፤ የ4 ፓርቲዎች ትብብር የሆነው ፓርቲው ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከሚያደርገው ቅስቀሳ ጎንለጎን ይህንን ጉዳይ በአጽንኦት እንደሚመለከተው ገልጸው፤ ጫፍና ጫፍ የወጡ አመለካከቶችን ወደ መካከለኛ መስመር በማምጣት የጋራ ሀገራዊ ራዕይ የመፍጠር ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል።

#አሐዱ


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2