ቆሻሻ ማስወገጃ እንዲቆፍር ተወሰነ‼️
የብልፅግና ፓርቲን ምርጫ ማስታወቂያን የቀደደ ተከሳሽ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ እንዲቆፍር ተወሰነበት
በሀድያ ዞን በጊምቢቹ ከተማ የሚኖረው ተከሳሽ ግንቦት 02 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ10 ሰዓት ተኩል ገደማ በጊምቢቹ ከተማ ልዩ ስሙ ቀጠና 03 መንደር 19 ተብሎ በሚጠራ አከባቢ በአንድ የሕክምና ተቋም ግድግዳ ላይ የተለጠፈውን የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት ማስታወቂያ መገንጠሉ ተገልጿል።
ድርጊቱን ሲፈፅም በዕለቱ ስምሪት ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት በሕግ ቁጥጥር ስር ሊውል እንደቻለ የከተማዋ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እስታውቋል
የግለሰቡ ድርጊት የፈፀመው ሆን ብሎ የምርጫ ሂደቱን ለማደናቀፍ በማሰብ በመሆኑም የጥፋተኝነት ፍርድ መሰጠቱ ተገልጿል።
በመሆኑም በቅጣት አወሳሰን መምሪያ መሠረት እርከን ሁለት ከ10 ቀን እስከ 6 ወር ቀላል እስር ወይም ከ10 ቀን እስከ 6 ወር የግዴታ ሥራ የሚያስቀጣ ሲሆን ፍ/ቤቱ የተከሳሽን ያለፈ የሕይወት ታሪክ የድርጊቱን አፈፃፀም ከግምት ውስጥ በማስገባት የግዴታ ሥራ አማራጭን ወስኖበታል።
በውሳኔው መሠረት ተከሳሽን ያርማል ያስተምራል ሌሎችን ያስጠነቅቃል በሚል ለሁለት ወራት፣ በሳምንት 3 ቀን በየዕለቱ 2:00 ሰዓት በጊምቢቹ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽህፈት ቤት አማካኝነት የሚሰራ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ጉድጓድ እንዲቆፍር በማለት ውሳኔ አስተላልፏል።
የጊምቢቹ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ዳኛ አቤነዘር ላምቦሬ በስተላለፉት መልዕክት፤ ወቅቱ የምርጫ ወቅት ስለሆነ ሕብረተሰቡ ማንኛውንም አይነት ከምርጫ ጋር ተያይዞ እንቅስቃሴዎችን በሚያደርጉበት ጊዜ ሕጉን በጠበቀ መልኩ ልሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።
@seledadotio

No comments yet.