23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ መጀመሩን ምክንያት በማድረግ ኮካ ኮላ ያዘጋጀው ልዩ የመክፈቻ ፕሮግራም ትላንት ማታ ሰኔ 05 ቀን 2

- Advertisement -
Sidebar AD

23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ መጀመሩን ምክንያት በማድረግ ኮካ ኮላ ያዘጋጀው ልዩ የመክፈቻ ፕሮግራም ትላንት ማታ ሰኔ 05 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል በደመቀ ሁኔታ ተካሄደ።

በዕለቱ የተገኙ የክብር እንግዶች በሜክሲኮ እና በደቡብ አፍሪካ መካከል የተደረገውን አጓጊ የዓለም ዋንጫ መክፈቻ ጨዋታ በዲኤስቲቪ (DStv) ተባባሪ አዘጋጅነት በትልቅ ስክሪን በአንድነት ተከታትለዋል።

ከዓለም ዋንጫ ጋር የ50 ዓመታት ረጅም የታሪክ አጋርነት ያለው ኮካ ኮላ (Coca-Cola) ያዘጋጀው ይህ ምሽት፣ የስፖርት አፍቃሪያንን እና ጥሪ የተደረገላቸውን እንግዶች በታላቅ ስሜት ያገናኘ ነበር።

ከተካሄደው የመክፈቻ ጨዋታ ጎን ለጎንም በዕለቱ የተገኙት ታዳሚዎች በተለያዩ አዝናኝ ስፖርታዊ ጨዋታዎች፣ ማራኪ የሙዚቃ ትዕይንቶች እና ልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች ምሽቱን በደስታ ሲያደምቁት አምሽተዋል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: