#Ethiopia | የብራዚሉ ክለብ ሳንቶስ ዛሬ በኮሪቲባ 3ለ0 በተሸነፈበት ጨዋታ ኔይማር በስህተት ተቀይሮ ወጥቷል።
በጨዋታው ወቅት ኔይማር የህክምና እርዳታ ለማግኘት ከሜዳው ወጥቶ መስመር ላይ ነበር።
ሳንቶስ ሮቢንሆን ለመቀየር መጠየቁን ተከትሎ አራተኛ ዳኛው በስህተት ውጪ ላይ ባለው ኔይማር ቀይረውታል።
አራተኛ ዳኛው የተጠየቀው ቅያሬ ውጪ ላይ ባለው ኔይማር ነው ብለው በማሰብ ስህተት ሰርተው ነበር።
ኔይማር ወደ ሜዳ ሊገባ ሲል መከልከሉን ተከትሎ በከፍተኛ ብስጭት ዳኛው ስህተት እንደሰራ ወረቀቱን ለካሜራ በማሳየት አሳውቋል።
ለ ዓለም ዋንጫ ምርጫ ራሱን ለማሳየት ጥረት ላይ የነበረው ኔይማር የተፈጠረው ስህተት ክፉኛ አስቆጥቶት ታይቷል።
ከጨዋታው በፊት የብራዚል ብሔራዊ መዝሙር በስታዲየሙ ሲሰማ ኔይማር ሲያለቅስ ታይቶ ነበር።
አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በነገው ዕለት የብሔራዊ ቡድኑን የዓለም ዋንጫ ስብስብ ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #Ethiopia
#tikvahethsport #sports
Source: GetuTemesgen









No comments yet.