ምክር ቤቱ ለቀብር የሚከፈልን ገንዘብ በ2,000 ብር ጭማሪ ማድረጉን አሳወቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት “ለህፃናት ቀብር ይከፈል የነበረው 1000 ብር ወደ 2000 ብር” ከፍ ማድረጉን አስታውቋል።

“ለአዋቂ ቀብር ደግሞ ይከፈል የነበረው 2000 ብር ወደ 4000 ብር” ከፍ መደረጉን ያሳወቀ ሲሆን፣ በርካቶች ደግሞ ጭማሪው የኑሮ ውድነትን ያላገናዘበ በሚል ቅሬታ እያቀረቡ ናቸው።

ም/ቤቱ ግን፣ የተደረገው የዋጋ ጭማሪ “የማህበረሰቡን ጫና የሚያቃልል ነው” ብሏል። ይህን የተረዱ አስተያየት ሰጭዎች ደግሞ፣ እንዴት ነው የክፍያ ጭማሪ “ጫና የሚያቃልለው?” የሚል ጥያቄ እያቀረቡ ናቸው።

የክፍያ ጭሚሪው “ከዚህ በፊት በአገልግሎት ክፍያ ውስጥ የማይካተተውን የብሎኬት አቅርቦት የሚጨምር” መሆኑን ገልጾ፣ “ይህም ማህበሰቡ ለብሎኬት ግዢ ያወጣ የነበረውን ከ1200 ብር እስከ 1800 ብር ወጪን የሚያስቀር” ነው ብሏል።

በአዲሱ ጭማሪ “አንድ ተገልጋይ የሚከፍለው 4,000 የብሎኬት አቅርቦቱን ጨምሮ ሁሉንም የቀብር አገልግሎት የሚጨምር” መሆኑን ገልጿል። “አንድ የቀብር ስነ ስርዓት ለማከናውን በትንሹ እስከ 28 ብሎኬት እንደሚያስፈልግ” የጠቀሰው ም/ቤቱ፣ “ከአዲሱ ማሻሻያ በኋላ ይህንን አቅርቦት መጅሊስ የሚፈጽመው ይሆናል” ብሏል።

“በዋጋ ማሻሻያ ላይ በበጎ ፍቃደኛነት የጀናዛ እጥበትና ሽኝት በማድረግ ለቀብር አገልግሎት በሚመጡ ተቋማት ላይ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ” አለመደረጉንም ባጋራው መረጃ አሳውቋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#Thiqah #AddisAbaba


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: