#FastMereja I በፈረንጆቹ የውድድር ዓመት ማጠናቀቂያ ላይ ስኬታማው የማንችስተር ሲቲ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከክለቡ ለመልቀቅ መወሰኑን የእንግሊዙ ‘ዘ ሰን’ ጋዜጣ የውስጥ ምንጮችን ጠቅሶ ዘገበ። በርካታ ታላላቅ ድሎችን ለክለቡ ያስገኘው ስፔናዊው አሰልጣኝ፣ የአሁኑ ውድድር ዓመት ሲጠናቀቅ ኮንትራቱን ላለማደስ መወሰኑ ነው የተነገረው።
ይህ የፔፕ ጋርዲዮላ ድንገተኛ ውሳኔ በማንችስተር ሲቲ ደጋፊዎችና በክለቡ አመራሮች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤን የፈጠረ ሲሆን፣ ክለቡ በቀጣይ የእሱን ምትክ ለመፈለግ አሁን ላይ አስገዳጅ ሁኔታ ውስጥ መግባቱ ተመልክቷል። ጋርዲዮላ ከሲቲ ጋር በነበረው ቆይታ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ጨምሮ በርካታ የፕሪሚየር ሊግ ክብረወሰኖችንና ስኬቶችን ማስመዝገብ የቻለ መሆኑ ይታወቃል።
ምንም እንኳን የ’ዘ ሰን’ ዘገባ የወጣቱንና የስኬታማውን አሰልጣኝ መልቀቅ በስፋት ቢያስተጋባውም፣ ከማንችስተር ሲቲ ክለብም ሆነ ከአሰልጣኙ በኩል እስካሁን ይፋዊ መግለጫ አልተሰጠም። ክለቡ የጋርዲዮላን ውሳኔ ለመቀልበስ የመጨረሻ ጥረት እያደረገ እንደሆነ የሚጠቁሙ መረጃዎች ቢኖሩም፣ አሰልጣኙ ግን አዲስ ፈተናን ለመጋፈጥ መወሰኑ በስፋት እየተነገረ ይገኛል።
Source: FastMereja








No comments yet.