#Ethiopia | አሜሪካ— የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ አንድ በሰንሰለት የታሰረ “መጻተኛ” (Alien) ከሳቸውና ከደህንነት አባላት ጋር ሲጓዝ የሚያሳይ ምስል በገዛ ማህበራዊ ሚዲያቸው “ትሩዝ ሶሻል” (Truth Social) ላይ በማጋራታቸው መነጋገሪያ ሆነዋል።
ምስሉ ዶናልድ ትራምፕን ከጥቁር መጻተኛ ጋር ጎን ለጎን ሲራመዱ የሚያሳይ ሲሆን፣ መጻተኛው እጁ በካቴና ታስሮ ይታያል።
ምስሉ በገሃድ የሚታይ እውነታ ሳይሆን በ AI (Artificial Intelligence) ቴክኖሎጂ የተቀናበረ መሆኑ ተረጋግጧል።
ምስሉ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በፍጥነት የተሰራጨ ሲሆን፣ ብዙዎች እንደ ቀልድ ቢመለከቱትም ሌሎች ደግሞ የቀድሞው ፕሬዝዳንት እንዲህ አይነት ምስሎችን ማጋራታቸው ለምን አስፈለገ? የሚል ጥያቄ እያነሱ ይገኛሉ።
“ይህ ምስል የቴክኖሎጂ ውጤት እንጂ እውነተኛ ክስተት አይደለም።”
የዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን ምስሉን ለምን ለማጋራት እንደመረጠ እስካሁን በይፋ የሰጠው ማብራሪያ የለም። ይሁን እንጂ ትራምፕ ከዚህ ቀደም መሰል አነጋጋሪ እና በቴክኖሎጂ የታገዙ ምስሎችን ለፖለቲካዊ መልዕክቶች እና ለደጋፊዎቻቸው መዝናኛነት ሲጠቀሙ ታይተዋል።
**#DonaldTrump #TruthSocial #AI #Alien #USPolitics #FakeImage**
Source: GetuTemesgen









No comments yet.