ኢትዮጵያ እንደ ዓለም ጤና ጉባኤ ያሉ አለም አቀፍ መድረኮችን በመጠቀም የጤና ዲፕሎማሲን በማጠናከር ላይ ትገኛለች – የጤና ሚኒ

- Advertisement -
Sidebar AD

ኢትዮጵያ እንደ ዓለም ጤና ጉባኤ ያሉ አለም አቀፍ መድረኮችን በመጠቀም የጤና ዲፕሎማሲን በማጠናከር ላይ ትገኛለች – የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ
___

#Ethiopia | በጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የተመራዉ የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን በ79 ነኛዉ የዓለም ጤና ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ስዊዘርላንድ ጄኔቫ ገብቷል።

ዶ/ር መቅደስ ለልዑካን ቡድኑ ኦሪየንቴሽን በሰጡት መድረክ እንደገለጹት ኢትዮጵያ በተለይም እንደ የዓለም ጤና ጉባኤ ያሉ አለም አቀፍ መድረኮችን በመጠቀም የጤና ዲፕሎማሲን በማጠናከር ላይ ትገኛለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት አባል ሀገር እንደመሆኗ በጉባኤዉ በሚወሰኑ ዉሳኔዎችና ቀጣይ ስራዎች የራሷን ድርሻ እንደምትወጣ ዶ/ር መቅደስ ተናግረዋል።

ወቅታዊ የኢቦላና ሀንታ ቫይረስ ሁኔታን ጨምሮ ሌሎች የዓለማችን ስጋት የሆኑ ወርሽኞችን መከላከልና መቆጣጠር በዋናነት በጉባኤዉ ቀርበዉ ዉይይት እንደሚደረግበት ይጠበቃል።

ከጉኤዉ ቀደም ብለዉ የዎክ ዘ ቶክ (Walk the Talk) ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን 79 ነኛው የዓለም ጤና ጉባኤ ከግንቦት 10-15 /2018 ዓ.ም በስዊዘርላድ ጄኔቫ እንደሚካሄድ ከወጣዉ ፕሮግራም ማወቅ ተችሏል።
(ጤና ሚ/ር)




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1