የዶላር ዋጋ ወደ 159.98 ብር ከፍ አለ፤ ብሔራዊ ባንክ ካቀረበው የውጭ ምንዛሬ ከእጥፍ በላይ ፍላጎት ቀረበበትአዲስ አበባ የ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የዶላር ዋጋ ወደ 159.98 ብር ከፍ አለ፤ ብሔራዊ ባንክ ካቀረበው የውጭ ምንዛሬ ከእጥፍ በላይ ፍላጎት ቀረበበት
አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባካሄደው ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ፣ የዶላር አማካይ የማሸነፊያ ዋጋ 159.98 ብር መድረሱን ይፋ አደረገ።
ባንኩ ይፋ ባደረገው መግለጫ መሠረት፣ በገበያው ውስጥ አሁንም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት መኖሩን የሚያሳዩ ውጤቶች ተመዝግበዋል።
ብሔራዊ ባንኩ ለዚህ ልዩ ጨረታ 500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ያቀረበ ቢሆንም፣ ከንግድ ባንኮች በኩል የቀረበው አጠቃላይ የፍላጎት መጠን ግን ከቀረበው አቅርቦት በእጥፍ በመጨመር 1.06 ቢሊዮን (አንድ ቢሊዮን ከስድሳ ሚሊዮን) ዶላር ሆኖ ተመዝግቧል።
በጨረታው ላይ በአጠቃላይ 30 የንግድ ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 14ቱ ባንኮች ብቻ ጨረታውን አሸንፈው የውጭ ምንዛሬውን ማግኘት ችለዋል።
የዕለቱ የምንዛሬ ተመን ዝርዝር፦
1. የማሸነፊያ አማካይ ክብደት ዋጋ (Weighted Average Rate): 159.9865 ብር
2. የመቁረጫ ዋጋ (Marginal/Cut-off Rate): 159.6299 ብር
3. ከፍተኛው የቀረበ የማሸነፊያ ዋጋ:160.9064 ብር
4. ዝቅተኛው የቀረበ የማሸነፊያ ዋጋ:157.3005 ብር
ብሔራዊ ባንክ ከሁለት ወራት በፊት ባካሄደው ተመሳሳይ ጨረታ 70 ሚሊዮን ዶላር አቅርቦ የነበረ ሲሆን፣ በወቅቱ የአንድ ዶላር አማካይ ዋጋ 157 ብር ከ46 ሳንቲም ሆኖ ማጠናቀቁ ይታወሳል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: