በአይራብ ዶኔሽን እና በጃተኒ አሊ ፋውንዴሽን የተዘጋጀው ይፋዊ የዲጂታል ገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ሊካሄድ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

📌ተቋማቱ የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ

#Ethiopia | ​በአይራብ ዶኔሽን እና በጃተኒ አሊ ፋውንዴሽን በጋራ የተዘጋጀው ይፋዊ የገቢ ማሰባሰቢያ የመክፈቻ ፕሮግራም በቅርቡ እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን፣ ሁለቱ ተቋማትም አብረው ለመሥራት የሚያስችላቸውን የጋራ ስምምነት በይፋ ተፈራርመዋል።

ይህ ልዩ መርሃ-ግብር ደህንነቱ በተጠበቀ፣ ግልጽነት ባለው እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በተደገፉ ዲጂታል የለጋሽነት መፍትሄዎች አማካኝነት፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰብአዊ እና ማህበረሰባዊ እገዛዎችን በዘላቂነት ለመደገፍ ያለመ ስትራቴጂካዊ የገቢ ማሰባሰብ አጋርነት መጀመሩን አብስረዋል።

በዕለቱም አይራብ ዶኔሽን የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ለጋሾች በቴሌብር ሱፐር አፕ እና በአይራብ ዶኔሽን ድረ-ገጽ አማካኝነት በቀላሉና በአስተማማኝ ሁኔታ መዋጮ ማድረግ የሚችሉበትን ምቹ ዲጂታል አሰራር በጉልህ የሚያሳይ ይሆናል።

​የአይራብ ቴክ ሶሉሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (AYRAB TECH SOLUTION PLC) መስራች አቶ ቢኒያም ፈቃዱ እና የጃተኒ አሊ ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር መሌቻ ሎጄ ህዝቡ እና የሚመለከተው አካል ሁሉ በዚህ ሰብአዊ ስራ ላይ ከጎናቸው እንዲሆንና አጋርነቱን እንዲያጠናክር ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ጃታኒ አሊ ፋውንዴሽን በአርቆ አሳቢው ሻለቃ ጃታኒ አሊ ማስታወሻነት የተመሰረተ ሲሆን፣ ማህበረሰቡ ራሱን እንዲችል፣ ጠንካራ የሆነ ማህበረሰብ እንዲገነባ እና ዘላቂ ልማት እንዲፈጠር በትምህርት፣ በውሃ፣ በጤና እና በማህበረሰብ አቅም ግንባታ ላይ በትጋት እየሰራ ነው።

ዛሬ የፋውንዴሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚና በተለያዩ ሀገር የሃላፊነት ቦታዎች የሚያገለግሉ ብዙ ግለሰቦች ሻለቃ ጃታኒ አሊ በተቋቋመው ትምህርት ቤት የተማሩ ሲሆን፣ ይህም የፋውንዴሽኑ ትውልድ የሚቀይር ራዕይ ህያው ማስረጃ ነው።

የእርስዎ ድጋፍ አንድ ልጅ እንዲማር፣ አንድ ቤተሰብ ተስፋ እንዲያገኝ እና አንድ ማህበረሰብ በራሱ እግር እንዲቆም ያግዛል።

ዛሬ ይቀላቀሉ ፣ ይደግፉ ፣ዘላቂ ለውጥ ይፍጠሩ። ሲሉ ጥሪያቸውንም አስተላልፈዋል።

እንዲሁም: በቴሌብር ሱፐር አፕ ላይ በሚገኘው አይራብ(AYRAB) አፕ ላይ እና በአይራብ ዶኔሽን ( https://donate.ayrabtech.com/ ) ሊንክ በመግባት በቀላሉ በሃገር ውስጥም ይሁን ከሃገር ውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮዽያ ወዳጆች በቀላሉ የፈለጉትን እና የቻሉትን ያህል መለገስ የሚችሉ መሆኑን አሳውቀዋል።

ይህንን ትልቅ ሰብአዊ እቅድ በይፋ ለመጀመር በሚሰናዳው በዚሁ ደማቅ መርሃ-ግብር ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ በጎ አድራጊዎች፣ የቢዝነስ መሪዎች፣ የሶሻል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ ታዋቂ የኢትዮጵያ ስብዕናዎች እና ከተለያዩ ዘርፎች የተወጣጡ ደጋፊዎች እንደሚገኙ ታውቋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
​#Ethiopia #AyrabDonation #JataniAliFoundation #DigitalFundraising #TechForGood #HumanitarianAid #Telebirr #AddisAbaba #SocialImpact #EthiopianNews






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: