በኤፕሪል 19 ቀን በማንቸስተር ሲቲ ስታዲየም ተካሂዶ በነበረው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ ለተከታታይ ወራት ሊጉን ሲመራ የነበረ

- Advertisement -
Sidebar AD

በኤፕሪል 19 ቀን በማንቸስተር ሲቲ ስታዲየም ተካሂዶ በነበረው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ ለተከታታይ ወራት ሊጉን ሲመራ የነበረው አርሰናል ፡ በማንቸስተር ሲቲ በገባበት ሁለት ጎል ተሸንፎ የወራት መሪነቱን ለሲቲ አስረከበ ።
……
እና የአርሰናል የዋንጫ ግስጋሴ የተገታ በመሰላቸው የአርሰናል ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ዘንድ ትልቅ ድንጋጤ ተፈጠረ

በዚህ ወቅት ታዲያ በሜዳው ውስጥ የነበረው የአርሰናሉ ኮከብ ዴክላን ራይስ ፡ ለቡድኑ መሪ ማርቲን ኦዲጋርድ አንድ ነገር ሲናገር በቲቪ ካሜራዎች ላይ ታየ ።
…..

ራይስ የተናገረው ቃል ” It’s not done” የሚል ነበር ።
……..
አርሰናሎች የነበራቸውን ሰፊ የነጥብ ብልጫ ቀስ በቀስ አጥተው ተስፋ በመቁረጥ ሜዳ ላይ ወድቀው በነበረበት ወቅት ዴክላን ራይስ ግን ነገሩ ገና እንደሆነ ፡ አሁንም የማሸነፍ እድል እንዳላቸው ፡ የሚያስረዳ ፡ ትልቅ ተስፋና ብርታትን የሚሰጥ መልእክት ያለው ንግግር ነበር የተናገረው ።
…….
ይህ የዴክላን ራይስ ንግግር ከተሰማ በኋላ ከእግር ኳስም አልፎ በብዙዎች ዘንድ መነቃቃትን እና ተስፋን የሚፈጥር ቃል ሆኖ ቆይቶ ዛሬ የአርሰናልን አሸናፊነት ተከትሎ ደግሞ እንደገና ቫይራል ሆኖ አምሽቷል ።

It’s not done”
…..
ራይስ ትክክል ነበር ። የአርሰናል ነገር ያለቀ ፡ ሽንፈቱ የተደመደመ አልነበረምና ፡ ከ22 አመታት ጥበቃ በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ማንሳት ችሏል ።
….
ይህ ከተሰማ ከደቂቃዎች በኋላም ዴክላን ራይስ በኢንስታግራም አካውንቱ የኛ ነገር ገና እንደሆነ ፡ ገና ብዙ ነገር እንደምናይ ነግሬያችሁ ነበር ፡ አሁን እደምንፈልገው ሆኖ ተጠናቋል ። የሚል ይዘት ያለው መልእክት አስተላልፏል
….
ከጥቂት ሳምንታት በፊት አርሰናላውያን ተስፋ ወደመቁረጥ እየገቡ ባሉበት ሰአት የተነገረው የዴክላን ራይስ ንግግር ስለኳስ ብቻ አይደለም ። ስለህይወትም ነው ።

It’s not done !

Via wasihun tesfaye



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: