አርሰናል ታሪካዊ ፍልሚያ ይጠበቅዋል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከበርንለይ ጋር ያደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ ስንመለከት ለመድፈኞቹ እጅግ ፈታኝና እስከመጨረሻዋ ሰከንድ ድረስ ከፍተኛ ጉልበት የጠየቀ ትንፋሽ አስጨራሽ ፍልሚያ እንደነበር ታዝበናል።

ይህ ጨዋታ በርካታ የእግር ኳስ አፍቃሪያንና ተንታኞች ቀድመው ከገመቱት በላይ ጠንካራ እንዲሆን ያደረጉ የራሱ የሆኑ ምክንያቶች ነበሩት።

ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ማነቆ ሆኖ የተመዘገበው የበርንሊ የተከላካይ መስመር ስልት ነው። ክለቡ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ካለበት አስቸጋሪ ሁኔታ ለመላቀቅና ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት ጨዋታውን የሞት ሽረት ትግል አድርጎት ነበር። ወደ ሜዳ የገቡትም ሙሉ በሙሉ መከላከል ላይ በማተኮርና የጨዋታውን ፍጥነት በመግታት የአርሰናልን የማጥቃት እንቅስቃሴ ለማሽመድመድ በማሰብ ነበር።

እንዲህ ዓይነቱ ጥልቅ የረብሻ መከላከል ስልት ደግሞ የትኛውንም ትልቅ ቡድን ክፉኛ እንደሚፈትን ይታወቃል።
ከሁሉም በላይ ግን የአርሰናል የአጥቂ መስመር የፈጠራ ብቃት ማነስ አንዱ ትልቅ ክፍተት ሆኖ ታይቷል።

መድፈኞቹ የኳስ ቁጥጥሩን የበላይነት ቢይዙም የበርንለይን የተቀናጀ መከላከል ሰብሮ ለመግባት የሚያስችሉ የፈጠራ ውሳኔዎች በመጀመሪያው አጋማሽ ጎልተው አልታዩም። በተለይ በክንፍ ተጫዋቾቻቸው ላይ የተደረገው ጥብቅ ክትትል አርሰናልን ከተለመደው የማጥቃት ጥንካሬው አግዶት አምሽቷል።

በአንፃሩ በርንለይ ጠንካራ አካላዊ ፍልሚያዎችን በመጠቀም በመልሶ ማጥቃትም ሆነ በአየር ላይ ኳሶች አርሰናልን ክፉኛ ፈትኖታል።

በተለይም በቆሙ ኳሶችና በማዕዘን ምቶች ወቅት በአርሰናል ተከላካዮች ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠር ችለዋል። ከዚህም በተጨማሪ በውድድር ዘመኑ ማጠቃለያ ላይ በመገኘታቸው በመድፈኞቹ ተጫዋቾች ላይ የታየው የአካል ብቃት መውረድና ድካም እንደ ልባቸው ፈጣንና ተለዋዋጭ ጨዋታ እንዳያሳዩ እንቅፋት ሆኖባቸዋል።

በአጠቃላይ ጨዋታው ማራኪ እግር ኳስ የታየበት ሳይሆን ታክቲካዊ ፉክክር የበረታበት ምሽት ነበር ማለት ይቻላል። ሆኖም መድፈኞቹ በእንዲህ ባሉ አስቸጋሪ አጋጣሚዎች የሚያሳዩት የውሳኔ ሰጪነት ብቃትና ትዕግስት ለዋንጫ ጉዟቸው እጅግ አስፈላጊ ነበር።

በዚህም መሰረት አርሰናል በርንሊን 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት በማሸነፍ የባለቤትነት ክብሩን ለመቀናጀት የአንድ ጨዋታ ድል ብቻ ነው የሚቀረው።

ይህንን ታላቅ ጉዞ ስንመለከትም በኩራት የምናጨበጭብበት ደማቅ ምሽት ሆኗል።

ምንጊዜም ድል ለመድፈኞቹ
ከአለባቸው ደሳለኝ አበሻ (ለንደን) 🇬🇧

#arsenal #football #premierleague #sports #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2