የኢራን የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ቀጥታ የስናይፐር እና የክላሽንኮቭ ስልጠና ማስተላለፍ ጀመሩ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በኢራን፣ በአሜሪካ እና በእስራኤል መካከል ያለው ወታደራዊ ፍጥጫ እና ውጥረት እጅግ አስፈሪ ደረጃ ላይ በደረሰበት በዚህ ወቅት፣ የኢራን ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች (IRIB) ታሪክ ከየቀኑ የዜና እወጃ ወጥተው የቀጥታ የስልጠና መድረክ መሆናቸውን ዓለም በደነገጠ ስሜት እየተከታተለው ይገኛል።

የጣቢያዎቹ የዜና አቅራቢዎችና ጋዜጠኞች ራሳቸው የጦር መሣሪያዎችን በአደባባይ በመያዝ እና የቀጥታ ተኩስ ልምምድ በማድረግ ላይ ናቸው።

በእነዚህ የቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭቶች ላይ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኘው የምሥራቅ ጀርመን ስሪት የሆነው እና በ7.62×39 ሚሊሜትር ጥይት የሚተኩሰው ‘MPi-KMS’ የተባለው የክላሽንኮቭ (AK-47) የጦር መሣሪያ ዓይነት ነው።

የቴሌቪዥን አቅራቢዎቹ የጦር መሣሪያውን እንዴት መፍታት፣ መግጠም፣ ጥይት መክተት እና ኢላማን መምታት እንደሚቻል ከእስላማዊ አብዮት ጥበቃ ጦር (IRGC) መኮንኖች ጋር በመሆን ለሕዝብ ቀጥታ ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።

ኢራን ይህንን ያልተለመደ የቴሌቪዥን ስርጭት “ሕይወትን ለኢራን መስዋዕት ማድረግ” (Sacrifice Life For Iran) ከሚለው አገር አቀፍ የዝግጁነት ዘመቻ ጋር ያገናኘችው ሲሆን፣ እስካሁን ድረስ ከ31 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በፈቃደኝነት ለዚህ የክተት ጥሪ መመዝገባቸውን የመንግስት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በቴህራን እና በኬርማንሻህ ከተሞች የሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች በአደባባዮች እና በመስጊዶች በተዘጋጁ ወታደራዊ ድንኳኖች ውስጥ የጦር መሣሪያ አያያዝ፣ የውጊያ ስልቶች እና የአገር መከላከያ ስልጠናዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ።

የኢራን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆኑት ሞህሴን ባርመህኒ የሀገሪቱ ሚዲያዎች ሙሉ በሙሉ “የጦርነት አቋም” (Wartime Posture) መያዝ እንዳለባቸው በይፋ ያወጁ ሲሆን፣ በአንድ የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ላይ የቴሌቪዥን አቅራቢው ክላሽንኮቭ መሣሪያውን ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) ባንዲራ አነጣጥሮ ሲተኩስ የታየበት ትዕይንት በባህረ ሰላጤው ሀገራት ዘንድ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ቁጣንና ውግዘትን አስከትሏል ሲል መናኸሪያ ኤፍ ኤም ዘግቧል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
#Iran #war #television
#usarmy #peace


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2