ከምርጫ በፊት 4ቱ የመጨረሻ ቀናት ላይ የምርጫ ቅስቀሳ እንደማይከናወን ያውቃሉ?

- Advertisement -
Sidebar AD

ምርጫ ከመከናወኑ በፊት ያሉት 4ቱ የመጨረሻ ቀናት የጥሞና ወቅት ይባላሉ።

የጥሞና ወቅት በቅድመ ምርጫ ዑደት ውስጥ የሚገኝ ጊዜ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ የምርጫ ዑደት መመሪያ መሠረት ምርጫ ከመደረጉ በፊት ያሉትን አራት ቀናት ያካትታል፡፡

በጥሞና ወቅት ታዲያ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ማለትም የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የመገናኛ ብዙኃን ሊተገብሯቸው የሚገቡ ኃላፊነቶች አሉ፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች፡-

1. የፖለቲካ ፓርቲ ዕጩዎችና ደጋፊዎቻቸው ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የሚያካሂዱት የምርጫ ውድድር እንቅስቃሴ ድምፅ መስጠት ከመጀመሩ ከአራት ቀን በፊት መጠናቀቅ አለበት፡፡

2. የፓለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው አራት ቀን ሲቀረው ማንኛውንም አይነት የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ አይፈቀድላቸውም፡፡ (በኢንተርኔት፣ በማኅበራዊ ሚዲያ፣ በግንባር፣ ቤት ለቤት፣ በአደባባይ ፣ በአዳራሽ ስብሰባ ምንም ዓይነት ቅስቀሳ ማከናወን በጥብቅ የተከለከለ ነው)

3. የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ጉዳዮች ዙሪያ አስተያየት ከመስጠት እንዲሁም ቃለ-መጠይቆችን ማድረግ አይፈቀድላቸውም።

4. የምረጫ ቦርዱ የሚያወጣቸውንም መመሪዎች ሊፈጽሙ ይገባል፡፡

ለመገናኛ ብዙኃን ተቋማት

1. የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት በጥሞና ወቅት ማንኛውንም ምርጫ ተኮር እንቅስቃሴዎችን ማሰራጨት አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም የፓለቲካ ፓርቲ ዕጩዎችን አግኝተው ቃለ-መጠይቆችን መሥራት አይፈቀድላቸውም፡፡

2. የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ከምርጫ ቦርድ የሚወጡ መረጃዎችን የማስተጋባት ኃላፊነት ሲኖርባቸው ከዚህ ውጪ በመመሪያዎች ላይ ያልተደነገጉ ተግባራትን እንዲፈጽሙ አይፈቀድላቸውም፡፡

ማናቸውም ምርጫን ለመከታተል ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የዕውቅና ባጅ የተሰጣቸው መገናኛ ብዙኃን ወይም ጋዜጠኞች እንደ አግባብነቱ በድምፅ ሰጪነት ለሚመዘገቡ፣ ለድምፅ ሰጪዎች እና ለዕጩ ወኪሎች ወይም ለታዛቢዎች ከምርጫ ጣቢያው ውጪ ቃለ-መጠይቅ የማድረግ መብት ይኖራቸዋል።

➡ ነገር ግን በምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ ቃለ-መጠይቅ ማድረግ የተከለከለ ነው።

EBC



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1