— ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ
#Ethiopia | በአዳማ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው “ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ ስኬት የመገናኛ ብዙሃን ሚና” በሚለው ታላቅ መድረክ ላይ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ መገናኛ ብዙሃን ከብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ አንጻር ስላላቸው ስትራቴጂካዊ ሚና ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን የመገናኛ ብዙሃን ታላቅ ሚና አስመልክቶ እንደተናገሩት ኢትዮጵያውያን በጋራ ሊቆሙ የሚችሉባቸው የብሔራዊ ጥቅም መዳረሻዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና ይህንን ግንዛቤ እንዲያጠናክሩ ለማድረግ ሚዲያው ቀዳሚውን ድርሻ ይይዛል ብለዋል።
አያይዘውም ከምርጫ ባሻገር ማየት ያስፈልጋል ካሉ በኋላ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የተመለከቱ ዘገባዎች ሲሰሩ፣ ሂደቱ የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚረዳ ዋነኛ መንገድ መሆኑን ሊያረጋግጥ በሚችል መልኩ መሆን አለበት። ጋዜጠኞች ምርጫን ሲዘግቡ “ከምርጫው ዕለት ባሻገር” ያለውን ሀገራዊ ሥዕል (ኢትዮጵያዊ አውድ) ማየት ይጠበቅባቸዋል።
የፓናል ውይይት በመድረኩ ላይ ከተሳታፊዎች በምርጫው ወቅት የሚዲያና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ቅንጅት የተመለከቱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታው ተስፋሁን ጎበዛይ አየር መንገድን፣ ባህር በርን ወይም ጂኦፖለቲካን ስንተነትን የምናነሳው ብሔራዊ ጥቅም፣ ልክ እንደ ምርጫ ባሉ ትልልቅ ሀገራዊ ሂደቶች ውስጥም ዋናው መለኪያ መሆን አለበት። ምርጫ የፓርቲዎች ፉክክር ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያ በጽኑ መሠረት ላይ እንድትቆም የምናደርግበት ሂደት ነው። ስለዚህ እያንዳንዱ የሚዲያ ባለሙያ የፖለቲካ ልዩነቶችን አክብሮ፣ ሀገርን በሚያቆሙ የጋራ ብሔራዊ ጥቅሞች ላይ ግንዛቤ የመፍጠር ግዴታ አለበት ሲሉ አሳስበዋል።
የኢዜአ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰይፈ ደርቤም መሰል የጋራ መድረኮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
#getu #NationalInterest #EthiopianElection2018 #MediaResponsibility #AdamaForum #7thGeneralElection #TesfahunGobezay #ENA #GovernmentCommunication #ብሔራዊጥቅም #7ኛውምርጫ #ሚዲያናሀገር #አዳማ #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen



Source: GetuTemesgen








No comments yet.