በምስራቅ አፍሪካ ከፍተኛ የዝናብ እጥረት ሊከሰት እንደሚችል ተገለፀ
ከመጪው ሐምሌ እስከ መስከረም ዓ.ም ባሉት የክረምት ወራት በኢትዮጵያ (በተለይም በመካከለኛው፣ ሰሜንና ምስራቅ አካባቢዎች) እንዲሁም በሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ በከፊል ኬንያና ኡጋንዳ ከተለመደው በታች የዝናብ እጥረት ሊከሰት እንደሚችል የኢጋድ አደጋ መከላከል ኃላፊ ዶክተር አሕመድ አምዲሆን አስጠነቀቁ።
በኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት እና በኢጋድ የአየር ጠባይ ትንበያ ማዕከል ትብብር በተዘጋጀው 73ኛው የምስራቅ አፍሪካ የአየር ጠባይ ትንተና እና ትንበያ ጉባኤ ላይ ይፋ እንደተደረገው፣ ቀጠናው ለአየር ንብረት ለውጥ እጅግ ተጋላጭ በመሆኑ ለዚህ ችግር ሊዳረግ ችሏል፤ ስለሆነም ሀገራቱ ከወዲሁ የውኃ እጥረት ከመከሰቱ በፊት ውኃን ማቆር፣ በአግባቡ መቆጠብ እና የውኃ እጥረት ወደሚታይባቸው አካባቢዎች አስቀድሞ ማጓጓዝን የመሰሉ ጠንካራ የቅድመ መከላከልና ጥንቃቄ ሥራዎችን በፈጣኑ መጀመር እንዳለባቸው ኃላፊው በጥብቅ አሳስበዋል።
@seledadotio

No comments yet.