በፋይዳ ማጣመር ስም እንዳይጭበረበሩደንበኞች የባንክ ሂሳባቸውን ከፋይዳ መታወቂያቸው ጋር እንዲያጣምሩ የተጀመረውን ሥራ አንዳንድ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በፋይዳ ማጣመር ስም እንዳይጭበረበሩ‼️
ደንበኞች የባንክ ሂሳባቸውን ከፋይዳ መታወቂያቸው ጋር እንዲያጣምሩ የተጀመረውን ሥራ አንዳንድ አጭበርባሪዎች እንደአጋጣሚ ለመጠቀም እየሞከሩ መሆኑ ተደርሶበታል።
በመሆኑም ደንበኞች የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች በማድረግ ራሳቸውን ከአጭበርባሪዎች እንዲከላከሉ ባንኩ አሳውቋል።
• በባንኩ ቅርንጫፎች በመገኘት ወይም ባንካችን ያዘጋጀውን የበይነ መረብ (Online) ማስተሳሰሪያ አማራጭ (https://cbefayda.cbe.com.et) በመጠቀም ብቻ የሂሳብ ቁጥርዎን ከፋይዳ መታወቂያዎ ጋር ያስተሳስሩ፤
• የማስተሳሰሩ ሥራ በስልክ ተደውሎ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ በሚላኩ መልእክቶች የማይሠራ መሆኑን ተገንዝበው መሰል ጥያቄዎችን አያስተናግዱ፤
• ባሉበት በበይነ መረብ ለማስተሳሰር ሲሞክሩ እርዳታ ከፈለጉ ከማያውቁት ወይም በሚገባ ከማያምኑት ሰው እገዛ አይጠይቁ።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1