ቶሚ ፕላስ አዲስ ቤት ከፈተ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ፕላቴዝ በጥንካሬ፣ በመተጣጠፍ፣ በሰውነት አቋም እና በአእምሮ እንዲሁም አካል ትስስር ላይ የሚያተኩር በዝቅተኛ ጫና የሚዘወተር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ነው።

በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ ዱባይና አሜሪካ ባሉ ሀገራት ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው የፕላቴዝ የስፖርት ዓይነት በቶማስ ኃይሉ/ቶሚ ፕላስ/ አማካኝነት በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ አገልግሎት መሰጠት ተጀምሯል።

ኢትዮ ፕላቴዝ ስቱዲዮ ​የተሰኝው ይህ አዲስ የስፖርት ማዕከል በተለይም ከወሊድ በኋላ ለሚመጡ የመገጣጠሚያ ችግሮች መፍትሄ በመስጠት፣ የሰውነት መተጣጠፍን በመጨመር እና የውስጥ የሰውነት ክፍሎችን በማጠንከር በኩል ከፍተኛ የጤና ጠቀሜታ እንዳለው ተገልጿል።

​ስፖርቱ በባህሪው የቅንጦት ቢሆንም፣ ማዕከሉ ውድ የሆኑ የስፖርት ማቴሪያሎችን እና በዘርፉ የተካኑ አሰልጣኞችን ከውጭ በማምጣት ማህበረሰቡን ባማከለና አቅም በሚፈቅደው ተመጣጣኝ ዋጋ ለማገልገል እየሰራ መሆኑን የማዕከሉ ባለቤት ቶማስ ኃይሉ/ቶሚ ፕላስ/ ገልጿል።

የተለመደው የፕላቴዝ ስፖርት በሴቶች የሚዘወተር ነው ሆኖም የአዲስ አበባው ማዕከል ለወንዶች ጭምር በልዩ ሁኔታ ቀርቧል።

​ማዕከሉ የመጀመሪያ ቅርንጫፉን በርካታ ሆቴሎች በሚገኙበትና የውጭ ቱሪስቶች መዳረሻ በሆነው ቦሌ አካባቢ የከፈተ ሲሆን፣ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ መደበኛ አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል።

ወደፊትም የደንበኞችን ተቀባይነትና ፍላጎት በማየት በሌሎች የክልል ከተሞች ቅርንጫፎቹን የማስፋፋት እቅድ እንዳለውም ተጠቁሟል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1