እስራኤል ለክሮሺያ የሰየመቻቸው አምባሳደር ውድቅ ተደረጉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የክሮሺያው ፕሬዝዳንት ዞራን ሚላኖቪች እስራኤል በጋዛና በሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ አካባቢዎች የምታካሂደውን ወታደራዊ ዘመቻ በግልጽ በመቃወም አዲሱን የእስራኤል አምባሳደር አንቀበልም ማለታቸው ታውቋል።

እስራኤል የአምባሳደሯ የሹመት ደብዳቤ መጽደቁን ሳታረጋግጥ አስቀድማ ይፋ ማድረጓ “ያልተጻፈ ዲፕሎማሲያዊ ህግን” የጣሰ ተግባር ነው ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ወቅሰዋል።

የፕሬዝዳንቱ ጽሕፈት ቤት ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ የተወከለው አምባሳደር የፕሬዝዳንቱን ፈቃድ ያላገኘ መሆኑንና ወደፊትም እንደማያገኝ በቁርጠኝነት አስታውቋል።

የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ፣ በክሮሺያ ዋና ከተማ ዛግሬብ የሚሾመውን ቀጣዩን አምባሳደር ሁኔታ ለመፍታት ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ውጥረት እየጨመረ የመጣ ሲሆን፣ አሜሪካና እስራኤል በቴህራን (ኢራን) የመንግስት ለውጥ ለማምጣት የሚያደርጉት ጥረት ከባድ የኢኮኖሚ ጉዳትና የረጅም ጊዜ ተፅዕኖ ሊያስከትል እንደሚችል ክሮሺያ አስጠንቅቃለች።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
#nbc #us #low
​#ክሮሺያ #እስራኤል #ዲፕሎማሲ #ጋዛ #ዞራንሚላኖቪች #ዜና


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2