የአሜሪካ ሴኔት በፕሬዝዳንት ትራምፕ ላይ ማዕቀብ የሚጥል ውሳኔ አሳለፈ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የአሜሪካ ሴኔት የሪፐብሊካኑን መሪ ዶናልድ ትራምፕን በግልጽ በመቃወም፣ የኢራንን ጦርነት ለማስቆም የሚያስችል የጦርነት ሥልጣን ውሳኔ ረቂቅ በድምፅ ብልጫ አጽድቋል።

የውሳኔ ረቂቁን ወደፊት ለማስኬድ በተደረገው የድምፅ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት 50 ለ 47 በሆነ ጠባብ ድምፅ ያለፈ ሲሆን 4 ሪፐብሊካኖች ከዲሞክራቶች ጋር በማበር ለውሳኔው ድጋፍ ሰጥተዋል።

አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት መሰንዘር ከጀመሩ ከ80 ቀናት በኋላ የተላለፈው ይህ ውሳኔ፣ ትራምፕ ከኮንግረሱ ፈቃድ ካላገኙ በስተቀር የአሜሪካ ጦር በኢራን ላይ የሚያደርገውን ድብደባ እንዲያቆም ያስገድዳል።

ይህ ውጤት በሕገ መንግሥቱ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው ወታደሮችን ወደ ጦርነት የመላክ ሥልጣን ሊኖረው የሚገባው ኮንግረሱ እንጂ ፕሬዝዳንቱ አይደሉም ብለው ሲከራከሩ ለነበሩት ሕግ አውጪዎች ትልቅ ድል ነው።

ይሁን እንጂ የውሳኔ ረቂቁ 100 አባላት ባሉት ሴኔት ውስጥ ቢጸድቅም በሪፐብሊካኖች በሚመራው የተወካዮች ምክር ቤት መጽደቅ ይኖርበታል።

በተጨማሪም ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሊጠቀሙበት የሚችሉትን ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ለማለፍ በሁለቱም ምክር ቤቶች የሁለት ሦስተኛ አብላጫ ድምፅ ማግኘት ግድ ይለዋል።

የውሳኔ ሃሳቡን ያቀረቡት ሴናተር ቲም ኬን፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን የቀረቡ የሰላም እና የዲፕሎማሲ ጥያቄዎችን ችላ በማለት ጦርነቱን እየቀጠሉ ነው ሲሉ ወቅሰዋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
#nbc #us #low


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: